Back

“በሀገራችን የተገነባው ዴሞክራሲዊ አንድነት የእግር እሳት የሆነባቸው የጥፋት ኃይሎች ሴራ መታግል ይባል ” ጓድ ሽፈራው ሽጉጤ የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት ኃላፊ

42ኛው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ(ህወሓት) የምስረታ በዓል የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት ሰራተኞችና አመራሮች በተገኙበት በድምቀት ተከበረ፡፡
 የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ጓድ ሽፈራው ሽጉጤ  ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ማንነት ማፈሪያ ከነበረበት እና  ፍትህ ከተጓደለበት ተላቀን ነፃነትና ፍትህ ለተጎናፀፍንበት ስርዓት የደረስነው የትግራይ ህዝብና ከአብራኩ የወጡ የህወሓት ታጋዮች በከፈሉት መስዋዕትነት መሆኑን ተናግረዋል፡፡  ‹‹በመሆኑ እስካሁን በነበረው ትግል አብረን እንደተሰለፍነው ሁሉ አሁንም ሁሉም ብሔራዊ ድርጅቶች ከህወሓት ጎን መቆማችንን በዚህ ታሪካዊ እለት ላይ ሆነን እናረጋግጣለን›› ብለዋል፡፡
በሀገራች የተመሰረተው ዴሞክራሲያዊ አንድነት  የእግር እሳት የሆነባቸው የጥፋት ኃይሎች  አንድነቱን ለመሸርሸር ቀን  ከለሊት እየሰሩ ይገኛሉ ያሉት ጓድ ሽፈራው ‹‹ መስመራችን ሃያል ህዝባችንም ፅኑ በመሆኑ አሁን በውስጣችን የተፈጠረውን ችግር በተሃድሷችን አርመን አንድነታችንን በፅኑ መሰረት ላይ እንገነባለን›› ሲሉም ተናግረዋል፡፡
በልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መስመር  እየተመራን በሀገር ደረጃ የተለያዩ ስኬቶችን መመዝገባቸውን የተናገሩት ጓድ ሽፈራው የትግራይ ክልል ህዝብም ለስኬቱ የሚጠበቅበትን እያበረከተ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል፡፡ "ለተከታታይ ሶስት ዓመታት እያጋጠመን የሚገኘውን የድርቅ አደጋ በራሳችን አቅም ምላሽ መስጠት የምንችልበት ደረጃ ላይ መድረሳችን ድህነትን ማሸነፍ እንደምንችል ያረጋጋጠ ነው"ም ብለዋል፡፡
ህወሓት የትጥቅ ትግል የጀመረበትን ዕለት ሲከበር  ሰማዕታት የተሰውለትን ዴሞክራሲ የሰፈነባት፣ ፍትህ የነገሳባት፣ የበለጸገ ህብረተሰብ የሚኖርባትና ተከባብሮ የመኖር እሴት የዳበረባት ሀገር እውን ለማድረግ በመረባረብ ሊሆን እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡  
የህወሓት ማዕከላይ ኮሚቴ በዓሉን ምክንክያት በማድረግ ባወጣው መግለጫ  የዘንድሮው 42ኛ አመት የህወሓት የምስረታ በዓል የተጀመረውን የጥልቅ ተሃድሶ ጉዞን በማጠናከር ሀገራዊ አንድነታችንን እና ልማታችንን ለማፋጠን ለህዝባችን ቃል የምንገባበት ነው መሆኑን አመልክቷል፡፡
ህወሓት በመሪ ድርጅቱ ህወሓት እየተመራ በወቅቱ በሀገሪቱ ተንሰራፍቶ የነበረውን ጨቋኝ ስርዓት ለመፋለም የትጥቅ ትግል  መጀመሩን ያስታወሰው መግለጫው  የትግሉ ግብ የድህነት ዘበኛ የነበረውን የደርግ ስርዓት ማስወገድ ብቻ ሳይሆን ሁሉም በእኩልነት የሚኖርባት ሀገር መገንባት እንደነበርና ይህ ማሳካት እንደተቻለም በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡
ህወሓት በየወቅቱ የሚያጋጥሙት ፈተናዎች በጽናት እያለፈ እዚህ መድረሱን ማዕከላይ ኮሚቴው ገልጾ የህዳሴው ተግዳሮቶች ለማሰወገድ ድርጅቱን በቀጣይነት ለማደስ የድርጅቱ አባላት ግንባር ቀደም ሚናቸው በአግባቡ እንዲወጡም ህወሓት ጥሪውን አቅርቧል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ከእህትና አጋር ድርጅቶ ጋር በመሆን  እንደከዚህ በፊቱ ሁሉ  ተጨማሪ አመርቂ ድሎን ለማስመዘግብ ህወሓት  ዝግጁ መሆኑን በመግለጫው ተመልክቷል፡፡
በእኩልነትና በመፈቃቀድ የተመሰረተው ፌዴራላዊ  ዴሞክራሲያዊ  ስርዓት የራስ ምታት የሆነባቸው ኃይሎች በህዝቦች መካከል ቅራኔና ልዩነትን ለመፍጠር ላይ ችች እያሉ መሆናቸው የገለጸው መግለጫው መላው የሀገራቸን ብሄሮች፣ ብሄረ ሰቦችና ህዝቦች ይህንን ተገንዘበው የእነዚህን እኩይ ኃይሎች ሴራ በማክሸፍ የተጀመረውን ህዳሴ ከዳር ለማድረስ የሚያደርጉትን ርብርብ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ማዕከላይ ኮሚቴው ጥሪውን አቅርቧል፡፡


ኢህአዴግ

ኢህአዴግ አገር የመምራት ሃላፊነትን ከተረከበ ጊዜ ጀምሮ ከውስጥም ከውጭም የሚነሱ በርካታ ውጣ ውረዶችን ያስተናገደ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጣጣምና የህዝባችንን ሁለንተናዊ መለወጥ ታሳቢ ያደረገ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ስርዓት በማራመድ በውጭ ሃይል ተፅእኖ የሚጠመዘዝ ድርጅት አለመሆኑን ገና በጠዋቱ በተግባር ያሳየ ድርጅት ነው፡፡

ከደርግ ውድቀት ማግስት አገራችን የመበታተን ስጋት ውስጥ የነበረችበት ሁኔታ ቢኖርም መላ የሃገሪቱን ህዝቦች በማስተባበርና በብስለት በመምራት ዴሞክራሲያዊ አንድነቷ በፅኑ መሰረት ላይ እየተገነባ እንዲዘልቅ አስችሏል። ህገ መንግስታችን የአንድነታችንና የመከባበራችን ማሰሪያ ውል እንዲሆን በሚያስችል መልኩ በህዝብ ሙሉ ተሳትፎ ተቀርፆ በመፅደቁ ያንን የመበታተን ስጋት ተሻግረን በጋራ ለዘላቂ ለውጥ መረባረብ ጀምረናል።

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሲያካሂድ የነበረውን ስብሰባ አጠናቀቀ

የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው አባልና በኢህአዴግ ፅህፈት ቤት የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪክ ጉዳዮች ሀላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ለኢቢሲ እንደተናገሩት፥ ኮሚቴው በወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የድርጅት ስራዎች እና የአመራር ቁመና ላይ ሀላፊነት በተሞላው መንገድ ህዝብና መንግስትን በሚያስቀጥል መልኩ ዝርዝርና ጥልቅ ግምገማዎችን አካሂዷል። በዚህ ድክመት ነው ያላቸውን በመለየት በዝርዝር መፍትሄዎችን ያስቀመጠው ኮሚቴው፥ ከሀገራዊ ለውጡ ጋር የመጡ በድክመት ያነሳቸውን ዝንባሌዎችን መመልከቱን ነው ያሱት።

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከነገ ጀምሮ ስብሰባውን ያካሂዳል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ) ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከነገ ነሓሴ 2 ቀን 2011 ም ጀምሮ ስብሰባውን የሚካሂድ ሲሆን በተለያዩ አጀንዳዎች እንደሚመክር ይጠብቃል፡፡ ኮሚቴ የድርጅት ስራዎች አፈጻጸምና በሌሎች ሀገራዊ ወቅታዊ አጀንዳዎች ላይ ውይይት እንደሚያካሄድ የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ሀገራዊ ምርጫው ጊዜውን ጠብቆ እንዲካሄድ አቋም እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስታወቁ።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን፥ ከጥያቄዎቹም ከምርጫ ጋር የተያያዘው አንዱ ነበር። በዚህም በሰጡት ምላሽ በአሁኑ ወቅት ምርጫ ይራዘም የሚሉ እና ወቅቱን ጠብቆ ይካሄድ የሚሉ የራሳቸው ምክንያት ያላቸው አካላት እንዳሉ አንስተዋል። ነገር ግን የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባደረገው ስብሰባው ምርጫ ከማካሄድ ጋር በተያያዘ በዝርዝር እንደተወያየበትና ምርጫው አይደረግም የሚል አቋም እንደሌለው አስታውቀዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

የፌዴራል ስርዓቱ ሁሉንም ፍላጎቶች ማስተናገድ የሚችል ነው!

እነአሜሪካና ስዊዘርላንድ ፌዴራላዊ ስርዓትን ተቀብለው መተግበር ከጀመሩ ምዕተ አመት አስቆጥረዋል። እንደተባለው ስርዓቱ ሀገርን አደጋ ውስጥ የሚጥልና አንድነትን የሚያጠፋ ቢሆን ኖሮ ዛሬ አሜሪካም ሆነ ስዊዘርላንድ የሚባሉ አገራትን ላናይ እንችል ነበር። አሜሪካ እ.ኤ.አ. በ1789 በህገመንግስት የተረጋገጠ ፌደራላዊ ስርዓትን በሀገሯ ላይ እውን አድርጋለች። ስዊዘርላንድ ደግሞ እ.ኤ.አ በ1848 ስርዓቱን በህገመንግስቷ እውቅና ሰጥታ ዘርግታለች። ጀርመንም እ.ኤ.አ.በ1871 ፌዴራላዊ መንግስትን ይፋ አድርጋለች። በመቀጠልም ካናዳ፣ ቤልጂየም፣ ህንድ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ናይጄሪያ፣ ሱዳን፣ አርጀንቲና፣ ብራዚል፣ ሜክሲኮ፣ የቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ የተለያዩ ግዛቶች፣ ቼኮስሎቫኪያ፣ ከኮሚኒዝም መፈራረስ በኋላ የቀድሞዋ ሶቪየት ህብረት ወደ ፌዴራል ስርዓት በሂደት እንደተቀላቀሉ የዘርፉ ምሁራን ከጻፏቸው ሰነዶች መረዳት ይቻላል።

ብርቅዬው ግድባችንን ከዳር ማድረስ-አማራጭ የሌለው ጉዳይ…!

ከስምንት ዓመታት በፊት መላ ኢትዮጵያውንን ቀልብ የሳበ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ተጀመረ፡፡ የአባይ ወንዝ ጥቅም ላይ አለመዋል በቁጭት ሲንገበገቡ የነበሩ መላው ኢትዮጵያውን ደስታቸው ወደር አጣ፡፡ ፕሮጀክቱ

ከ‹‹እኔ ብቻ›› ስሜት መሻገር ይገባል!!

በመደመር እሳቤ የጀመርነው ሁሉን አቀፍ አገራዊ ለውጥ እንደ ንብ ታታሪ ሆኖ በመስራት ለውጡን ዳር ማድረስ ከሁሉም ዜጋ የሚጠበቅ ሀላፊነት ነው፡፡ በእኛነት ስሜት በመደራጀት በአገራችን ይስተዋሉ የነበሩ ችግሮችን በጋራ በመታገል ዛሬ የደረስንበት ለውጥ እንዲመጣ ማድረግ ተችሏል፡፡ በተባበረ አንድነታችን ያቀነቀንለት የለውጥ ዝማሬ አልፎ አልፎ አንዳንድ መሰናክሎች እያስተናገደ ይገኛል፡፡ በቁልቁለት መንገድ ለማስገባት ከኋላ የሚገፉ ከፊት የሚስቡ የራሳቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ የሚሯራጡ ሃይሎች እዚም እዚያም ይስተዋላሉ፡፡ የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ ወደ ኋላ ለመመለስ በርካታ ወጥመዶች እየዘረጉ ይገኛሉ፡፡ በብሄሮች መካከል ያለውን ልዩነት በማጉላት በሕዝቦች መካከል ጭቅጭቅና ንትርክ ለመፍጠር የተለያዩ ሙከራዎችን ሲያደርጉ ይስተዋላሉ፡፡ በበርካታ ውጣውረድ ታልፎ የተገኘውን የለውጥ ጉዞ ለማስቀጠል አልፎ አልፎ የሚፈጠሩ ችግሮችን በሠለጠነ እና በሰከነ መንገድ በመፍታት የዴሞክራሲ ባህላችንንም ማሳደግ ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡

Visitorcounter Visitorcounter

Today       

542

       የዛሬ ጎብኚ

Yesterday       

1120

       የትናንት ጎብኚ

This Month       

9379

       የዚህ ወር ጎብኚ

This Year       

236985

       የዚህ ዓመት ጎብኚ

Total        

364976

       አጠቃላይ ጎብኚ