መጣጥፎች መጣጥፎች

ሙስናን መከላከል የሁሉም ህብረተሰብ ኃላፊነት ነው!!

በአለማችን ሙስና የማይነካው ሀገርና ህዝብ የለም፡፡ ጥቂት የህዝብ ቁጥር ካላቸው ሀገራት ጀምሮ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥርና የቆዳ ሽፋን ባላቸው ሀገራት ጭምር ሙስና የሁሉም ችግር ሆኖ የሚታይ ነው፡፡ በአፍሪካ ሙስና እና የሙስና ተግባር ከቅኝ ግዛት በፊት ጀምሮ የነበረ ቢሆንም አህጉራችን በቀኝ ግዛት ስር ወድቃ በነበረችበት ወቅት ባዕዳውያን ተልዕኳቸውን ለማስፈጸምና ለማቀላጠፍ ለተላላኪዎች በሚሰጡት ጉርሻ ተጀምሮ ወደ ተለመደና ጉዳዮችን ከማስፈፀም ጀረባ መሟላት ያለበት ቅደመ ሁኔታ ሆኖ ዘለቀ፡፡

ኮሽ ሲል- ፌደራሊዝም?

ከሰሞኑ ሀገራችን እየተከተለችው ባለው የዴሞክራሲያዊ ፌዴራላዊ ስርዓት ላይ የተለያዩ ኃሳቦች በመሰንዘር ላይ ናቸው፡፡ በአንድ በኩል ስርዓቱን የሚያብጠለጥሉ ኃይሎች ብቅ ብቅ እያሉ ነው፡፡ በተለይም በፖለቲካ ፓርቲና በጋዜጠኝነት ስም የታቀፉ አንዳንድ ወገኖች በስርዓቱ ላይ ‹‹ድሮም ብለን ነበር›› የሚል ይዘት ያላቸው መረጃዎች በማሰራጨት ላይ ይገኛሉ፡፡

30 የሆነው በምክነያት ነው!

አገር ሰላም ብለው ቤተሰባቸውን በፍቅር ተሰናብተው ቸር ያውለን፤ ቸር ያውላችሁ ተባብለው ወደ ጉዳዮቻቸው ተፍ ተፍ ሲሉ ማስተዋል በተሳነው፤ ኃላፊነት በጎደለው አሽከርካሪ የመኪና አደጋ ደርሶባቸው ካሰቡበት ሳይደርሱ መንገድ ላይ የቀሩትን ዜጎች ቤት ይቁጠራቸው፡፡ ማለዳ ሁሉም የራዲዮ ጣቢያዎች ማለት ይቻላል ወሬያቸው ሁላ የትራፊክ አደጋን በተመለከተ ነው፡፡

የስኬቶች ሁሉ መሰረት

የተለያዩ አካላት ትምህርት ዓለምን የመለወጥ አቅም ያለው መተኪያ የሌለው መሳሪያ እንደሆነ በተለያየ አጋጣሚ ሲናገሩ ይሰማል፡፡ በህዝቦችና በአገራት መካከል የስልጣኔ ልዩነት እንዲፈጠር ያደረገውም እያንዳንዱ ግለሰብም ሆነ አገር ለትምህርት በሚሰጠው ትኩረት፤ ትምህርትን ለማሳፋፋትም ሆነ ራሱን በትምህርት ለማነፅ ባለው ቁርጠኝነት መሆኑን የዓለም ነባራዊ ሁኔታ ያሳያል፡፡

ለአፍሪካ ተምሳሌት የሆነች ሀገር

መንግስታት ሉዓላዊነታቸውን ከወራሪ ኃይል ለመጠበቅ ጠንካራ የመከላከያና ወታደራዊ ኃይል ያስፈልጋቸዋል፡፡ በተጨማሪም መሪዎች ጠንካራ መንግስት ለመመስረት እንዲያስችላቸው ግዛታቸውን ለማስፋፋት ያላቸው ወታደራዊ ኃይል ከጥንት ጊዜ ጀምሮ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡