መጣጥፎች መጣጥፎች

በውሃው ያስተሳሰረን አባይ በልማቱም ያቆራኘናል!

በአለማችን ከ165 በላይ ዋናዋና ወንዞች ይገኛሉ፡፡ ከነዚህ መካከል በርዝመት የናይል (አባይ) ወንዝን የሚስተካከል የለም፡፡ በሚይዘው የውሃ መጠን ቀዳሚ ደረጃ የያዘውን የአማዞን ወንዝን አንኳን ናይል በበርካታ ኪሎሜትሮች ይበልጠዋል፡፡ ይህ ወንዝ ስያሜውን ‹ኒሎስ› ከሚለው የግሪክ ቃል ያገኘ ሲሆን፤ በአረብኛው ባህር አል ኒል ተብሎ ይጠራል፡፡

ለበለጠ ስኬት የምንተጋበት የከፍታ ዓመት

አሮጌውን ዓመት ሸኝተን አዲሱን ዓመት ከተቀበልን ቀናት ተቆጥረዋል፡፡ በያዝነው ዓመት ለአገራችን የስኬትና የብልፅግና፤ ለህዝባችንም የለውጥ ዘመን ይሆን ዘንድ መንግስትና ህዝብ ዓመቱን በብሩህ ተስፋ ተቀብለውታል፡፡ የከፍታና የመለወጥ ዘመን ይሆን ዘንድ እጅ ለእጅ ተያይዘው ለመትመም ቃላቸውን አድሰው ተፍ ተፍ በማለት ላይ ይገኛሉ፡፡ የትናንት ስኬታችን ወደላቀ ምዕራፍ የሚሸጋገርበት፤ ዛሬንና የወደፊቱን የምናቅድበት፤ ውጥናችንን ለማሳካት የምንተጋበት ዓመት ነው 2010፡፡

የሀገር ፍቅር

የሀገር ፍቅር (Patriotism) ስለሀገራችን የሚሰማን ጥልቅ ስሜት፣ በልባችን ውስጥ የታተመ የትስስርና የእኔነት ስነ ልቦና እና ይህንን ማንነት ለመጠበቅ እስካስፈለገ ድረስ ምንም አይነት ፈተናን ለመጋፈጥ አቅም የሚሆነን ውስጣዊ ሃይል ነው። ይህ ስሜት በአንድ ሀገር ውስጥ ስለተወለድን ብቻ የሚሰማን (default option) ሳይሆን ለሀገርና ለወገን በመኖርና ራስን አሳልፎ በመስጠት በተግባር የሚገለጽ የፍቅር አይነት ነው።

የማህበራዊ ዘርፍ ስኬት ሲለካ

ሀገራችን የቀደምት ስልጣኔ መነሻ ከሚባሉት እንደነ ቻይና፣ ግብጽ፣ፋርስ የመሳሳሉት ጋር የምትመደብ ናት፡፡ እንደነ ላሊበላ ወቅር አብያተ ክርስትያናትና የአክሱም ሀውልት የመሳሰሉ የስልጣኔ አሻራዎች ይህንኑ የሚያረጋግጡ ናቸው፡፡ እነዚህ ሶስት ሺህ ዓመታት በላይ እድሜ ያላቸው ቅርሶች የሀገርቷ ስልጣኔ ጥንታዊ መሆኑንና ቅርሶቹ ይዞታቸውን ጠብቀው ከትውልድ ትውልድ መተላለፋቸው በወቅቱ የነበረው ትውልድ በእውቀት መመራቱን የሚያመላክት ነው፡፡

ለከፍታው ዘመን መደላደል የተፈጠረባቸው ዓመታት

መስከረም 1 ቀን 2000 ዓ.ም ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን የተለመደው የዘመን መለወጫ ቀን ብቻ አልነበረም፡፡ ይልቁንም አንደኛውን ሚሊንየም ሸኝተው ሌላኛውን ሚሊንየም የሚቀበሉበት ብሎም ከአንደኛው ወደ ቀጣዩ ክፍለ ዘመን መሸጋገሪያ ዘመን በመሆኑ ኢትዮጵያውያን በተለየ ስሜት ውስጥ ሆነው ነበር ይህንን ቀን የተቀበሉት፡፡ በርግጥም ሺህ ዓመታትን ቆጥሮ የሚመጣውን ሚሊንየም ለማየት መታደል ልዩ ደስታን ይፈጥራል፡፡ ይህ እድለኝነትም ጭምር ነው፡፡