መጣጥፎች መጣጥፎች

ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ጠበቆች ነን

የአለም ሙቀት መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ይገኛል፡፡ እንደ የአለም ሜትሮሎጂካል ድርጅት/WMO/ መረጃ የአለም ሙቀት መጨመር ከቅድመ ኢንዱስትሪያል ጊዜ ከ 0.5 ከኢንዱስትሪያል ዘመን በኋላ በ2016 ወደ 1.1 በዲግሪ ሴልሽየስ ደርሷል፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ሰዓት ያደጉ ሀገራት ሳይቀር የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ውጤት በሆኑት በኤልኒኖ እና ላኒና መዘዝ ምክንያት በጎርፍ መጥለቅለቅና በድርቅ መጠቃት የተለመደ የዓለማችን ክስተት ሆኗል፡፡

የሰላም ዋጋ ውድ ነው!

ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት ነው፡፡ ለዚህም ነው ሰዎች ሲገናኙ ቅድሚያ ስለ ሰላማቸው ሁኔታ የሚጠያየቁት፡፡ ጠዋት ከእንቅላፋቸው ተነስተው‹‹በሳላም አውለኝ›› ማታ ሲተኙም›› በሰላም ያዋልከኝ በሰላም አሳድረኝ›› ብለው ምስጋናቸውን የሚገልጹም የሰላምን ትልቅ ዋጋ በመረዳት ነው፡፡ እናም ሁሉም ሰው ሊባል በሚችል መልኩ ሰላም በህይወቱ ላይ ትልቁን ዋጋ ያለው ውድ ነገር መሆኑን ይገነዘባል፡፡

የታላቁ ሰው አሻራዎች ሲታወሱ

የታላቁ ሰው የህይወት ጉዞ የአፍሪካ የነጻነት አድባር የሆነውን ሰንሰለታማውን የአድዋ ተራሮች ጥግ ከምትገኘው የአድዋ ከተማ በ1947 ዓ.ም ጀመረ፡፡ ወላጅ አባቱ ተምሮ ሀኪም እንዲሆን ብርቱ ፍላጎት ነበራቸው፡፡ የብላቴናው የትምህርት ውጤትም የአባቱን ተስፋ ይበልጥ አለመለመዉ፡፡

መለስ ሰብአዊ ፣ ዲሞክራሲያዊ ፣ ፍትሃዊ መሪ !!

1947 ዓ.ም በወርሃ ግንቦት መባቻ በትግራይ ክልል በአድዋ ከተማ የህፃን ልጅ ለቅሶ የመወለድ ብስራትን ይዞ ብቅ አለ ፡፡ በዚያች የጥቁር ህዝብ ነፃነት ምድር ተምሳሌት በሆነችዉ አድዋ ታሪክ ራሱን ለመድገም ያሰበ መሆኑን ማንም የገመተው አይመስልም ፤ ያኔ ነበር ታላቁ መሪ ወደዚች አለም የተቀላቀለው ፡፡ ስለታላቁ መሪ መለስ ብዙ ሲባል ሰምተናል ፤ ተብሏልም ፡፡

ግብር የዜግነት ግዴታ ብቻ ሳይሆን ባህልም መሆን አለበት!

በተደጋጋሚ እንደሚገለፀው ከግብር የሚሰበሰብ ገቢ መሰረት ልማት መገንባትን ጨምሮ የአንድ ሀገር ዜጎችን ሁለንተናዊ ፍላጎት ለማሟላትና ሀገራዊ እድገትን ለማፋጠን ወሳኝ ነው፡፡ በአውሮፓና በአሜሪካም ሆነ በአጭር አመታት ፈጣን እድገት በማስመዝገብ ወደበለፀጉ ሀገራት በተሸጋገሩ እንደ ደቡብ ኮሪያና ሲንጋፓር ባሉ የኢስያ ሀገራት ግብርን በወቅቱ መክፈል የዜግነት ግዴታ ብቻ ሳይሆን ባህላቸው መሆኑን እንመለከታለን፡፡