መጣጥፎች መጣጥፎች

ተምሳሌታዊ እርምጃ

ተፈጥሮ ውብ ናት፡፡ በአለም ላይ ለሰው ልጆች የመንፈስ እርካታ ምንጭና የአይን ማረፊያ የሆኑ ኃብቶችን አብርክታለች፡፡ ዛፎች፣ እንስሳት፣ አየሩ፣ ውሃው፣ ፏፏቴው፣ አዕዋፋት፣ የበረዶ ክምር፣ የመሬት አቀማመጥ ወዘተ ሁሉም ለዓለማችን የተበረከቱ የተፈጥሮ ውብ ስጦታዎች ናቸው፡፡ ምድራችንን ከዚነህ ኃብቶቿና ገጽታዋ ውጭ ምድረበዳ ሆና ማሰብ ይጨንቃል፡፡

የጤና ፖሊሲያችን የስኬታችን ማሳያ ነው

በሀገራችን ‹‹ልጅ ይወለድ እንጂ በእድሉ ያድጋል" የሚለው አባባል ከድሮ ጀምሮ በማህበረሰባችን ዘንድ የተለመደና አሁንም ድረስ በገጠሩ ማህበረሰብ ዘንድ የተለመደ ጉዳይ ነው፡፡ ከዚህም አኳያ የሚወለዱ ልጆች በተመጣጣነ ምግብ እጥረትና ንፅህና ጉድለት ምክንያት ለተላላፊ በሽታዎች የመጠቃት እድላቸው ሰፊ የነበረበት ሁኔታ እንደነበር ይታወቃል፡፡

መሪር ትዝታዎቻችን ስደትን ለመጠየፍ ከበቂ በላይ ናቸው

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አይንና ጆሯችን ያለው ሳውዲ አረቢያ ላይ ሆኗል፡፡ ሁላችንም ዜጎቻችን ምንም እንግልት ሳይደርስባቸው ለሀገራቸው ምድር እንዲበቁ ምኞታችን ነውና ልክ እንደ ወላድ ቀን መቁጠሩን ተያይዘንዋል፡፡ ኢትዮጵያውያን በተናጠልም ተደራጅተውም ወንድም እህቶቻቸውን ‹‹ያለፈው ይበቃናል፤ ዳግም በደላችሁን መስማትም አንፈልግም፤ እባካችሁ ኑልን›› እያሉ ናቸው፡፡

የወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለሁለንተናዊ እድገት

ባለፉት የድሮ ስርዓታት የተረጋጋ ሰላምና ዴሞክራሲ ባለመኖሩ ምክንያት ወጣቶች አስከፊ ግፍ እየደረሰባቸው ባልፈለጉት አላማ እየተሰለፉ እስከ የህይወት መስዋእትነት ይከፍሉ ነበር፡፡ ራዕያቸውም ተጨናግፎ የጨለማ ጉዞ እጣ ፈንታቸው ሆኖ ቆይቷል፡፡ ለብዙ ዘመናት በአምባገነናዊና በገዥ መደቦች እጅ በመውደቃቸው ምክንያት የሀገራችንን መፃኢ እድል ሊቀይር የሚችለው ወጣት ሃይል በከንቱ እንዲባክን ተፈርዶበት ነበር፡፡

ከማጀት እስከ ጦር ግንባር የተፈተነ ጥንካሬ!

ሴት የቤተሰብና የትውልድ መሰረት ናት፡፡ ሴት የፍቅር መገለጫ ናት፡፡ ደግነትና ሆደ ሰፊነት በሴት ይወከላል፡፡ ለነገሩማ ሀገርስ በሴት አይደል የምትሰየመው፡፡ ማህበረሰባችንም ገደብ የሌለውን መውደድና ፍቅር ለመግለጽ ወንዶችን ጭምር በሴት ጾታ አንቺ፤ እሷ ብሎ መጠራራት የተለመደ ነው፡፡ ከሁሉ በላይ ደግሞ ሴት የሰላም መገለጫ ናት፡፡ እንዲያውም ይህንን ሰላማዊ ሁኔታ ለመግለጽ አንዳንድ ምሁራን ዓለም በሴቶች ብትመራ በየቦታው የሚከሰቱ አለመግባባቶችና ግጭቶች እንደማይፈጠሩ ያትታሉ፡፡