መጣጥፎች መጣጥፎች

ስንዴውን ከእንክርዳዱ እንለይ….

የማህበራዊ ትስስር ገጾች ጥቅምና ጉዳት በሀገራችንም የሚታይ ነው፡፡ የውሸት ዜናዎች ለግጭት መንስኤዎች ሲሆኑ ይስተዋላል፡፡ በተዋቂ ሰው ስም የሚከፈቱ የውሸት ገጾች የተሳሳቱ መልዕክቶች ሲያስተላልፉ ይታያል፡፡ ከፍተኛ የመንግስት ባለ ስልጣኖች ያልተናገሩት፤ ስዎችን የሚያሳዝንና ወደ መጥፎ ድርጊት የሚያነሳሱ መረጃዎች በውሸት ተቦክተው ይጋገረሉ፡፡ በአንድ አካባቢ ማንነትን ወይም ኃይማኖትን ማእከል ያደረገ ጥቃት እንደደረሰ የውሸት ዜናዎችን በማስተጋባት ሌሎች ተመሳሳይ የአጸፋ እርምጃ እንዲወስዱ ያነሳሳሉ፡፡ የሰዎችን ክብርና ስም የሚያጠፉ እና በህዝብ ዘንድ ያላቸውን ቅቡልነት የሚሸረሽሩ ሀሰተኛ ዜናዎቸ እንዲህ በብዛት እንዲሰራጩ ደደረጋል፡፡ በአጠቃላይ ሀሰተኛ ዜናዎች በዓለማችንም ይሁን በሀገራችን አሳሳቢ እየሆኑ ነው፡፡ የሰዎችን አብሮ የመኖር እሴት እንዲሸረሸር በማደረግ በተቃራኒው አለመተማመንና ግጭት እንዲከሰት ምክንያት እየሆኑ ነው፡፡ የውሸት ዜናዎችን ለመከላከል መንግስታት፣ የማህበራዊ ትስስር ባለ ቤቶችና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የራሳቸውን ጥረት እያደረጉ ነው፡፡ ይሁንና አድማሱን እያሰፋ የመጣው የሀሰት መረጃዎችን ችግር ለመከላከል ሁሉም ኃላፊነት አለበት፡፡ በመጀመርያ ራሳችን የሀሰት መረጃዎችን ከማሰራጨት መራቅ እናም ሌሎች የሚያሰራጩትንም መከላከል ይገባል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የውሸት ዜናዎችን ከማጋለጥ ጀምሮ አንድ መረጃ ስናይ እውነታውን ለማረጋገጥ ዝግጁ መሆን፤ በተለያዩ አቅጣጫዎች መመልከታና እውነትነታቸውን በአስተውሎት መመርመር ያስፈልጋል፡፡ እውነታውን ሳናረጋገጥ ለሌሎች አለማጋራት ይገባል፡፡ ስንዴውን ከእንክርዳዱ ለይተን በጎ በጎውን መውሰድ መጥፎውን ማራገፍ ይገባል፡፡ የውሸት መረጃ አቀናባሪዎችን መከላከል የምንችለው ይህንን ስናደርግ ብቻ ነው፡፡

ብርቅዬው ግድባችንን ከዳር ማድረስ-አማራጭ የሌለው ጉዳይ…!

ከስምንት ዓመታት በፊት መላ ኢትዮጵያውንን ቀልብ የሳበ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ተጀመረ፡፡ የአባይ ወንዝ ጥቅም ላይ አለመዋል በቁጭት ሲንገበገቡ የነበሩ መላው ኢትዮጵያውን ደስታቸው ወደር አጣ፡፡ ፕሮጀክቱ

አንድ ቤት የሚገነቡ….

አንዳንዴ አባቶቻችን በተረትና በምሳሌያዊ አነጋገር ያወረሱን አባባሎች በጣም የልብ አድርስ ናቸው፡፡ አሁን እየሆነ ያለውን ነገር ሳስበው ከነዚህ ተረቶች መካከል ‘’አንድ ቤት የሚገነባ ሳር አይሰራረቅም’’ የሚለው በህሊናዬ አቃጫለ፡፡ ሃቅ ነው፡፡ አንዲት ጎጆ ቤት በጋራ እየገነቡ ያሉ ሰዎች እንዴት ብሎ ለጣሪያ ክዳን የሚሆናቸውን ሳር ይሰራረቃሉ፡፡ ባይሆን ተባብረው ቆንጆና ጠንካራ ሳር ካለበት ፈላልገው ያመጣሉ እንጂ፡፡ ይህን እንዳነሳ ምክንያት የሆነኝ በአገራችን የሚስተዋለው የመጓተትና በተለያየ ጎራ የመፈራረጅ አባዜ የተጠናወተው መብዛቱ ነው፡፡ አንዱ የአንዱን ቡድን ወይም ወገን ስም እየጠራ ያወግዛል፣ አንዱ የሌላኛውን አካባቢ ሰው እየጠራ ጠላትህ ነው እያለ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ በቀልና ጥላቻን ይሰብካል፡፡ ማህበራዊ ሚዲያ ደግሞ ይህንን መርዝ ለመርጨት የሚጠቀሙበት ሰፊ ምህዳር እየሆነ መጥቷል፡፡

ሀገር ወዳድነት ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት በመያዝ ይገለፃል

ሁላችንም እንደምናውቀው በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት መግቢያ ላይ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በራሳቸው ፈቃድ ላይ ተመስርተው ጠንካራ የጋራ ኢኮኖሚና አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ ለመገንባት ቃል ኪዳን ስለመግባታቸው ሰፍሯል፡፡ ይህ ደግሞ በአንድ አገር ለሚመዘገበው ሁለንተናዊ ልማትና የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የሕዝቡ የላቀ ተሳትፎ የማይተካ ሚና እንዳለው የሚያመላክት ነው፡፡ ሕዝብ ሳያምንበትና ሳይቀበለው የሚጀመሩ ማናቸውም ልማቶች እንዲሁም የሰላምና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ከዳር እንደማይደርሱ ግልፅ ነው፡፡ በኢህአዴግ መሪነት አሁን በሀገራችን እየታየ ያለው ለውጥና ለውጡን ተከትሎ የተፈጠሩ መነቃቃቶችም ኢህአዴግ በ11ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ ካስቀመጠው አቅጣጫ የመነጩ ናቸው፡፡ ይህ ድርጅታዊ ውሳኔ ኢህአዴግ ሀገር በመራባቸው ዓመታት ያስመዘገባቸውን ስኬቶችንና የተፈጠሩ ክፍተቶችንም በሚገባ በመገምገም በቀጣይ እንደ ሀገር በጋራ ጉዳዮች ላይ ብሔራዊ መግባባትን በማስፈን ወደ ህዝብ ተጠግቶ ለመስራት የሚያስችለውን ሁኔታ የፈጠረለት ነው፡፡

ከሁሉም በፊት የሀገር ሰላም ይቅደም!

''ሰላም'' የሚለው የአማርኛ ቃል ከጦርነትና አመፅ ነጻ መሆን ከሚለው የአንዳንድ መዝገበ ቃላት ፍቺ የዘለለ ትርጉም አለው። የቃሉ ምንጭ “ሻሎም'' የሚለው የእብራይስጥ ሥርወ ቃል ሲሆን በሰዎች ህይወት ውስጥ ተሟልቶ መገኘት የሚገባውን ደህንነት፣ ምሉዕነት፣ ፍፁምነትና ዋስትናን የሚያመለክት ሰፊ ፅንሰ ሐሳብ የያዘ ነው። ሰላም ማግኘት የሚቻለው ፍትህና ማህበራዊ መረጋጋት በሰፈነበት የፖለቲካ ስርዓት ውስጥ መኖር ሲቻል ነው። በአጠቃላይ ሠላም ማለት ሰዎች በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ፣ በማህበራዊና መንፈሳዊ ዘርፎች ውስጥ ዋስትና ያለውን ህይወት የሚመሩበት የሰከነ ስርዓት እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል።