መጣጥፎች መጣጥፎች

ፕራይቬታይዜሸን ለምን?

የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በቅርቡ መደበኛ ስብሰባውን ካካሄደ በኋላ በአበይት ጉዳዮች ላይ አቅጣጫዎችን ያስቀመጠ መሆኑ ይታወቃል:: ሰሞኑን የአገራችን አበይት አጀንዳ ሆኖ አለም እየተነጋገረበት ያለው የኤርትራና የኢትዮጵያ አዲስ የሰላም ግንኙነትን ጨምሮ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ያስተላለፋቸው ውሳኔዎች መሬት እየያዙ እየሄዱ መሆኑን መመልከት ይቻላል፡፡

ከአስመራ እስከ አዲስ አበባ የተዘረጋ የማያረጅ የፍቅር ሸማ

"ተዛወሪ አውቶብሰይ ተዛወሪየ አስመራ ሸዋ ኾይኑ መፋቐርየ፡፡ ኮሚደረ ፀቢሒ አቡንየ ሰላምን ፍቐርን ዘይብሉ አይጥዕሙንየ፡፡ ተዛወሪ ነፋሪት ነፋሪትየ አክሱም መቐለ ኾይኑ መፋቐርየ፡፡"

አዲስ የሰላምና የፍቅር ድልድይ ተገንብቷል

የኤርትራው ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂን ጨምሮ በርካታ የሀገሪቱ ባለ ስልጣናት አስመራ በሚገኘው የአውሮፕላን ማረፍያ ውስጥ እንግዶችን በመጠባበቅ ላይ ናቸው፡፡ በሁሉም ዘንድ ጉጉትና ተስፋ ይታያል፡፡ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶር አብይ አሕመድንና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን የያዘው አየር በባንዲራችን ባሸበረቀው ጭራና ክንፍ ደመናውን እየሰነጠቀ በአስመራ ሰማይ እየጋለበ ነው፡፡

የሰው ዘር መገኛ-በለውጥ መንገድ ላይ

ከአዲስ አበባ ተነስትን ጉዟችንን ወደ ደቡብ ምሥራቅ አቅጣጫ አድርገናል፡፡ በርካታ ኪሎ ሜትሮችን አቆራርጠን ኮረብታና ዳገት የናፈቁት የሚመስለውን የአዋሽ አርባን መንገድ ተከትለን ሙቀት ብርድልብሷ ወደ ሆነው አፋር መዳረሻችንን አደረግን፡፡ እንቁላል እንደታቀፈች ዶሮ ሰብሰብ ያሉ ባህላዊ ጎጆዎች ተመለከትን፡፡

መደመር……..ብዝሃነታችንን አክብረን ለአንድነታችን መትጋት

የሰኔ ዝናብ ገና ከጅምሩ ከብዶ ነው የጀመረው፡፡ የሌሊቱ ዶፍ የጠዋቱ ብርድ ልብስ ደራርበው እንኳን አጥንት ድረስ ዘልቆ ይገባል፡፡ እለት ቅዳሜ ሰኔ 16/2010 ከተማዋ ገና በማለዳው በጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ ምስል ያሻበረቁ ቲሸርት በለበሱ ሚሊየኖች አሸብርቃለች፡፡