ትኩስ ዜና

የኢትዮጵያና ጂቡቲ ህዝቦች ግንኙነትን ለማጠናከር የሁለቱ አገራት መሪ ፓርቲዎች አብረው እንደሚሰሩ ኢህአዴግ ገለጸ፡፡ ምክር ቤቱ የብሔራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፀደቋል፡፡ ምክር ቤቱ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፀደቀ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤት አባላቱ የተነሱ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ በቀጣይ ሊጉን የሚመሩ ወጣቶችን መረጠ የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ በአሁን ሰአት በውቢቷ ሀዋሳ ከተማ በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ 4ተኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ከጥር 19 ቀን ጀምሮ በሀዋሣ ከተማ ሊካሄድ ነው፡፡ የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታዎችን በዝርዝር ገምግሞ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መደበኛ ስብሰባውን አጠናቋል። ግዴታዬን እወጣለሁ፤ መብቴንም እጠይቃለሁ” በሚል መሪ ቃል ሃገራዊ የገቢ ንቅናቄ ተጀመረ፡፡ የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ በመቐለ ከተማ እያካሄደ ባለው የሊጉ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ጓዲት መሰረት መስቀሌን ከደኢህዴን በሊቀመንበርነት፣እንዲሁም ጓዲት መስከረም አበበን ከአዴፓ ምክትል ሊቀ መንበር አድርጎ መርጧል። የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ የአገሪቱን ሰላም በማስጠበቅ ሂደት ውስጥ ግንባር ቀደም ሆኖ ለመንቀሳቀስ መወሰኑ ተገለፀ በኢሕአዴግ ምክር ቤት ፅ/ቤት ምክትል ሃላፊ ጓድ መለስ አለሙ የሚመራው የድርጅታችን የልኡካን ቡድን የቻይና ጉብኝት እንደቀጠለ ነው የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በዛሬው እለት በደማቅ የመክፈቻ ስነስርአት በመቐለ ከተማ ተጀምሯል ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከ30 የአውሮፓ አገራት አምባሳደሮች ጋር የኢትዮጵያን የለውጥ ምዕራፍ በተመለከተ ዛሬ ታህሳስ 5 ቀን 2011 በጽ/ቤታቸው ውይይት እያካሄዱ ነው:: በጓድ አቶ መለሰ አለሙ የኢህአዴግ ጽ/ቤት ም/ሀላፊ ሚኒስትር የተመራ የልኡካን ቡድን በቻይና የስራ ጉብኝት እያደረገ ነው። አብሮነት፣ መቻቻልና ሰላም ታላቅ ሀገር ለመገንባት ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ። የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን የኢትዮጵያዊነትን ልዩ ልዩ ፀጋዎች እያሳየን፣ እያከበርንና እየጠበቅን የምናከብረው በዓል ነው - ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ 13ኛው የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀንን በአዲስ አበባ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ ነው የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች ጽህፈት ቤቱ ተልዕከውን በተጠናከረ መልኩ መወጣት በሚችልበት ሁኔታ ላይ በዛሬው ዕለት ውይይት አካሂደዋል፡፡ “የምንናገረው ዴሞክራሲ የምንኖርበት መሆን አለበት” ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ

ጉባኤ ጉባኤ

Back

የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ በቀጣይ ሊጉን የሚመሩ ወጣቶችን መረጠ

በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ያለው የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ ጉባኤ ወጣት አስፋው ተክሌን የሊጉ ሊቀመንበር ወጣት አክሊሉ ታደሰን ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር አድረጎ መረጠ፡፡ አመራሮቹ ሊጉን ለቀጣይ ሁለት ዓመት ተኩል የሚመሩ ይሆናል፡፡

ጉባኤው ባካሄደው ስብሰባ የሊጉን ያለፉትን የሁለት ዓመት ተኩል የሥራ አፈጻጸም ሪፓርት ላይ ውይይት ያካሄደ ሲሆን የደቡብ ኮሪያ የወጣቶች ልምድ ተሞክሮ መቅሰም እንዲቻል በሰነድ መልክ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በውይይቱ በርካታ ጥያቄዎች ተነስተው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን የወጣቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ጉዳዮች፣ የማንነትና የወሰን ጉዳዮች፣ ተጀመረውን አገራዊ ለውጥ በሚመለከት እንዲሁም ሊጉ ከእናት ድርጅቱ ጋር ያለውን ግንኙነት የተመለከቱ ጥያቄዎች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ፣ የወጣቱ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም እንዲሁም አገራዊነት አንድነትን አስተሳሰብ የሚያጎለብቱ ሥራዎች መሰራት እንደሚያስፈልግ የጋራ መግባባት ተደርሶባቸዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ አገራችንን የተጀመሪውን አገራዊ ለውጥ ወደ ፊት ለማስቀጠል የሊግ አደረጃጀቶች ከመቸውም ጊዜ በላይ አጠናክረው መስራት እንደሚጠበቅባቸው በውይይቱ ተነስቷል፡፡ ወጣቶች በሕዝቦች መካከል ቁርሾን ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ አካላትን በጋራ መታገል እንደሚገባም ተመላክቷል፡፡

የሊጉ ሊቀ መንበሩ ወጣት አስፋው ተክሌ ባስተላለፈው መልዕክት በአገራችን ተጀመረውን ለውጥ ለማስጠል ሚያጋጥሙ እንቅፋቶችን በጋራ መታገል ይገባል ብለዋል፡፡

ሊቀመንበሩ በመልዕክታቸው አለበት አፈጻጸም ለወደ ተሸለ ምዕራፍ ለማሻገር ከመቸውም ጊዜ በላይ አጠናክረን መስራት አለበት ብለዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የህግ በላይነትን ለማረጋገጥ ሊጋችን ከፍተኛውን ድርሻ መውሰድ አለበት ብለዋል፡፡ እንዲሁም ከልዩነት ይልቅ አገራዊ አንድነት አስተሳሰብን የሚያጠናክሩ ሥራዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም ገልጸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለሁለት ዓመት ተኩል የኦዲትና ቁጥጥር ኮሚሽን አባላትንም ምርጫ አካሂዷል፡፡ በመጨሻም ጉባኤው የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል፡፡


ቪዲዮ ቪዲዮ

Visitor counter Visitor counter

Today       

833

       የዛሬ ጎብኚ

Yesterday       

5826

       የትናንት ጎብኚ

This Month       

43845

       የዚህ ወር ጎብኚ

This Year       

196003

       የዚህ ዓመት ጎብኚ

Total        

300577

       አጠቃላይ ጎብኚ