Back

“የምንናገረው ዴሞክራሲ የምንኖርበት መሆን አለበት” ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ

በሀገራችን ዴሞክራሲ ባህል በማሳደግና የዴሞክራሲ ግንባታን በማጠናከር ዘላቂ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት እንደሚገባ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገለጹ፡፡  በፖለቲካ ድርጅቶች መካከል በሀገራዊ ጉዳዮች ዙርያ የሚደረጉ ውይይቶች አካሄድ የተመለከተ ውይይት  በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ተካሂዷል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚካሄደውን ውይይትና አጠቃላይ የሀገራችን የዴሞክራሲ ሁኔታ የሚመለከት ገለጻ አድርገዋል፡፡  
ዶክተር አብይ በገለጻቸው የሀገራችን የደሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ አዝጋሚ እንደሆነ በመግለጽ ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱን ለማጠናከር እንዲረባረቡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በሀገራችን ስለ ዴሞክራሲ የሚወራውን ያህል ተግባራዊ እንዳልተደረገ በመግለጽ "የምንናገረው ዴሞክራሲ የምንኖርበት መሆን አለበት" ሲሉም ተናግረዋል፡፡ ሁሉም ፓርቲዎች አገርንና ህዝብን አስቀድመው በፖለቲካ ውድድር ማሸነፍና መሸነፍ እንዳለ መገንዘብ ይኖርባቸዋል ሲሉም ነው የገለጹት፡፡
በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል በሚደረገው ወይይት ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች መሳተፍ እንደሚገባቸው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሀገራችን ያሉት ከ70 በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተቀራራቢ የፖለቲካ ዓላማ ያላቸው በአንድ ላይ በመሰባሰብ ወደ ሶስት ወይ አራት ዝቅ ቢሉ የበለጠ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለማጠናከር ጠቃሚ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡ ህዝብንና ሀገርን ተጠቃሚ እንደሚያደርግም አመልክተዋል፡፡
ቀጣዩን ሀገር አቀፍ ምርጫ ነጻና ፍትሃዊ ለማድረግ የሚያስፈልጉ የህግ ማሻሻያዎችና ተቋማዊ ለውጦች ላይ ያተኮሩ ውይይቶች ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
የህዝብ ተቀባይነት ያላቸው የደሞክራሲያዊ ተቋማት ከመገንባት ጎን ለጎን የህዝቡን ዴሞክራሲያዊ ባህል የሚያሳድጉ ስራዎችን በቀጣይነት መስራት እንደሚገባም አመልክተዋል፡፡ የመገናኛ ብዙኃን  የዴሞክራሲ ባህል በማሳደግ ረገድ የጎላ ሚና እንዳላቸውም አስገንዝበዋል፡፡
በውይይቱ የተሳተፉ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች በበኩላቸው ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት በትብብር መንፈስ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ቁጥር በርከት ማለት ለሀራችን ብዙም የማይጠቅም በመሆኑ በውይይትና መግባባት ውህደቶችን በመፈጸም ቁጥሩን መቀነስ ተመራጭ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

 


ጉባኤ ጉባኤ

የኢትዮጵያና ጂቡቲ ህዝቦች ግንኙነትን ለማጠናከር የሁለቱ አገራት መሪ ፓርቲዎች አብረው እንደሚሰሩ ኢህአዴግ ገለጸ፡፡

የጂቡቲ መሪ ፓርቲ ራሊ ፎር ፒፕልስ ኮንግረስ (RPP) 40ኛ የመስረታ በዓል ባለፈው ሰኞ በጂቡቲ ተከብሯል። በክብረ በዓሉ ላይ በኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም የተመራው የኢህአዴግ ልዑካን ቡድንም ታድሟል። በመድረኩ ንግግር ያደረጉት አቶ ብናልፍ ፎር ፒፕልስ ኮንግረስ ፓርቲ ባለፉት 40 አመታት ውስጥ የህዝብን ህይወት ከማሻሻልና በቀጠናው ኢኮኖሚያዊ ትስስር እንዲሁም ሰላም ከማረጋገጥ አኳያ ላስመዘገባቸው ድሎች ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

ምክር ቤቱ የብሔራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፀደቋል፡፡

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት እያካሄደ ባለው መደበኛ ስብሰባ የብሔራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላትን ሹመት አጽድቋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

ምክር ቤቱ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፀደቀ

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት እያካሄደ ባለው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 24ኛ መደበኛ ስብሰባ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፅደቀ።

ተጨማሪ ያንብቡ…

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤት አባላቱ የተነሱ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤት አባላቱ የተነሱ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ እድገቱን በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚንስትር ዶር አብይ የሀገሪቱ መደበኛ ኢኮኖሚ ጤናማ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ በቀጣይ ሊጉን የሚመሩ ወጣቶችን መረጠ

በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ያለው የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ ጉባኤ ወጣት አስፋው ተክሌን የሊጉ ሊቀመንበር ወጣት አክሊሉ ታደሰን ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር አድረጎ መረጠ፡፡ አመራሮቹ ሊጉን ለቀጣይ ሁለት ዓመት ተኩል የሚመሩ ይሆናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ በአሁን ሰአት በውቢቷ ሀዋሳ ከተማ በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ በአሁን ሰአት በውቢቷ ሀዋሳ ከተማ በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በጉባኤ ላይ የእለቱ የክብር እንግዶች የደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳደር የተከበሩ አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ እንዲሁም የኢህአዴግ ምክር ቤት ፅ/ቤት ሀላፊ ጓድ ብናልፍ አንዷለምን ጨምሮ በርካታ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ 4ተኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ከጥር 19 ቀን ጀምሮ በሀዋሣ ከተማ ሊካሄድ ነው፡፡

በኢሕአዴግ ወጣቶች ሊግ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ጉባኤ ከሁለት ዓመት እስከ ሁለት አመት ተኩል ጊዜ መካሄድ ይኖርበታል፡፡ በዚሁ መሰረት የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ ከጥር 19-21 /2011 ዓ.ም 4ተኛ ድርጅታዊ ጉባኤውን በሀዋሣ ከተማ ያካሂዳል፡፡ የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ ሥራ አስፈጻሚ አባልና የአዘጋጅ ኮሚቴው ቃል አቀባይ ወጣት ጫላ ኦሊቃ የጉባኤውን ዝግጅት አስመልክቶ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ጉባዔው ከእናት ድርጅቱ ጉባኤ ማግስትና ሀገሪቱ በሁለንተናዊ የለውጥ እንቅስቀሴ ባለችበት ወቅት የሚካሄድ በመሆኑ ታሪካዊና ልዩ ያደርገዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ቪዲዮ ቪዲዮ

Visitor counter Visitor counter

Today       

330

       የዛሬ ጎብኚ

Yesterday       

5826

       የትናንት ጎብኚ

This Month       

43342

       የዚህ ወር ጎብኚ

This Year       

195500

       የዚህ ዓመት ጎብኚ

Total        

300074

       አጠቃላይ ጎብኚ