Back

የኢትዮጵያና ጂቡቲ ህዝቦች ግንኙነትን ለማጠናከር የሁለቱ አገራት መሪ ፓርቲዎች አብረው እንደሚሰሩ ኢህአዴግ ገለጸ፡፡

የጂቡቲ መሪ ፓርቲ ራሊ ፎር ፒፕልስ ኮንግረስ (RPP) 40 የመስረታ በዓል ባለፈው ሰኞ በጂቡቲ ተከብሯል። በክብረ በዓሉ ላይ በኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም የተመራው የኢህአዴግ ልዑካን ቡድንም ታድሟል።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት አቶ ብናልፍ ፎር ፒፕልስ ኮንግረስ ፓርቲ ባለፉት 40 አመታት ውስጥ የህዝብን ህይወት ከማሻሻልና በቀጠናው ኢኮኖሚያዊ ትስስር እንዲሁም ሰላም ከማረጋገጥ አኳያ ላስመዘገባቸው ድሎች ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

የኢትዮጵያና የጂቡቲ ህዝቦችች ተመሳሳይ ማንነትና የኑሮ ዘይቤ እንዳላቸው የገለጹት የጽህፈት ቤት ሃላፊው ሁለቱ አገራት በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካና በማህበራዊ መስተጋብሮች የተሳሰሩና የአንዱ መኖር ለሌላኛው ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። በመሆኑም በአንዱ በኩል የሚመጣው ስኬትም ሆነ ውድቀት በሌላኛው ላይ የሚኖረው ተጽኖ ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡ የሁለቱ አገራት ህዝቦች እጣ ፋንታ የተሳሰረ እንደሆነ የገለጹት አቶ ብናልፍ ኢህአዴግ ከአገሪቱ መሪ ፓርቲ ጋር በመሆን የሁለቱን ህዝቦች ኑሮ ማሻሻል ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አመራርና የመደመር ፍልስፍናቸው ስር አገሪቱ በመሪው ፓርቲ ኢህአዴግ ሁሉን አቀፍ ሪፎርም እያካሄደች መሆኑን የተናገሩት አቶ ብናልፍ በአሁኑ ወቅትም አመርቂ ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆኑን ገልጸዋል።

የመደመር ፍልስፍናው ከአገራዊ አንድነት ባለፈ በምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ ትስስርን ለማምጣት ያለመ በመሆኑ አብሮ ለመስራት ትልቅ እድል የሚሰጥ መሆኑንም አክለዋል።
በመሆኑም ድርጅታቸው ኢህአዴግ የሁለቱን አገራትና ህዝቦች ተስስር ለማጠናከር ከጂቡቲው መሪ ፓርቲ ጋር በትብብር መስራቱን አጠናክሮ አንደሚቀጥል አቶ ብናልፍ አረጋግጠዋል።
የኢህአዴግ የልዑካን ቡድን አባላት ቀጠናዊ ትስስርን በተመለከተ ከጂቡቲ፣ ኬኒያ፣ ሩዋንዳ፣ ሶማሊ ላንድ፣ ታንዛኒያ፣ ሱዳንና ሶማሌ ጋር የጋራ ምክክር አድረገዋል።

ምክክሩም ቀጠናዊ ትስስር በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እንዴት ማዳበር እንደሚገባና መሪ ፓርቲዎች በዚህ ስራ ውስጥ የሚኖራቸውን ሚና በአግባቡ የዳሰሰ ነበር።
ልዑኩ የጂቡቲ ወደብንና አገልግሎት አሰጣጡን የጎበኘ ሲሆን ከተለያዩ የመንግስትና የፓርቲ ስራ ሃላፊዎች ጋር ስለ ሁለቱ አገራት ግንኙነት መክሯል።

 


ጉባኤ ጉባኤ

የኢትዮጵያና ጂቡቲ ህዝቦች ግንኙነትን ለማጠናከር የሁለቱ አገራት መሪ ፓርቲዎች አብረው እንደሚሰሩ ኢህአዴግ ገለጸ፡፡

የጂቡቲ መሪ ፓርቲ ራሊ ፎር ፒፕልስ ኮንግረስ (RPP) 40ኛ የመስረታ በዓል ባለፈው ሰኞ በጂቡቲ ተከብሯል። በክብረ በዓሉ ላይ በኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም የተመራው የኢህአዴግ ልዑካን ቡድንም ታድሟል። በመድረኩ ንግግር ያደረጉት አቶ ብናልፍ ፎር ፒፕልስ ኮንግረስ ፓርቲ ባለፉት 40 አመታት ውስጥ የህዝብን ህይወት ከማሻሻልና በቀጠናው ኢኮኖሚያዊ ትስስር እንዲሁም ሰላም ከማረጋገጥ አኳያ ላስመዘገባቸው ድሎች ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

ምክር ቤቱ የብሔራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፀደቋል፡፡

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት እያካሄደ ባለው መደበኛ ስብሰባ የብሔራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላትን ሹመት አጽድቋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

ምክር ቤቱ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፀደቀ

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት እያካሄደ ባለው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 24ኛ መደበኛ ስብሰባ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፅደቀ።

ተጨማሪ ያንብቡ…

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤት አባላቱ የተነሱ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤት አባላቱ የተነሱ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ እድገቱን በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚንስትር ዶር አብይ የሀገሪቱ መደበኛ ኢኮኖሚ ጤናማ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ በቀጣይ ሊጉን የሚመሩ ወጣቶችን መረጠ

በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ያለው የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ ጉባኤ ወጣት አስፋው ተክሌን የሊጉ ሊቀመንበር ወጣት አክሊሉ ታደሰን ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር አድረጎ መረጠ፡፡ አመራሮቹ ሊጉን ለቀጣይ ሁለት ዓመት ተኩል የሚመሩ ይሆናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ በአሁን ሰአት በውቢቷ ሀዋሳ ከተማ በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ በአሁን ሰአት በውቢቷ ሀዋሳ ከተማ በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በጉባኤ ላይ የእለቱ የክብር እንግዶች የደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳደር የተከበሩ አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ እንዲሁም የኢህአዴግ ምክር ቤት ፅ/ቤት ሀላፊ ጓድ ብናልፍ አንዷለምን ጨምሮ በርካታ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ 4ተኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ከጥር 19 ቀን ጀምሮ በሀዋሣ ከተማ ሊካሄድ ነው፡፡

በኢሕአዴግ ወጣቶች ሊግ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ጉባኤ ከሁለት ዓመት እስከ ሁለት አመት ተኩል ጊዜ መካሄድ ይኖርበታል፡፡ በዚሁ መሰረት የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ ከጥር 19-21 /2011 ዓ.ም 4ተኛ ድርጅታዊ ጉባኤውን በሀዋሣ ከተማ ያካሂዳል፡፡ የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ ሥራ አስፈጻሚ አባልና የአዘጋጅ ኮሚቴው ቃል አቀባይ ወጣት ጫላ ኦሊቃ የጉባኤውን ዝግጅት አስመልክቶ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ጉባዔው ከእናት ድርጅቱ ጉባኤ ማግስትና ሀገሪቱ በሁለንተናዊ የለውጥ እንቅስቀሴ ባለችበት ወቅት የሚካሄድ በመሆኑ ታሪካዊና ልዩ ያደርገዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ቪዲዮ ቪዲዮ

Visitor counter Visitor counter

Today       

344

       የዛሬ ጎብኚ

Yesterday       

5826

       የትናንት ጎብኚ

This Month       

43356

       የዚህ ወር ጎብኚ

This Year       

195514

       የዚህ ዓመት ጎብኚ

Total        

300088

       አጠቃላይ ጎብኚ