Back

ኢህአዴግ የውስጠ ድርጅት ጥንካሬውን በማጎልበት የመልካም አስተዳደር ችግርን ለመቅረፍ የሚያስችለውን አቅጣጫ ተቀመጠ

ኢህአዴግ  የውስጠ ድርጅት ጥንካሬውን በማጎልበት የመልካም አስተዳደር ችግርን ለመቅረፍ የሚያስችለውን አቅጣጫ ተቀመጠ
«ህዝባዊ አደራን በላቀ እድገትና ትራንስፎርሜሽን» በሚል መሪ ቃል በመ‚ለ ከተማ  ለአራት ቀናት በድምቀት ሲካሄድ የቆየው የኢህአዴግ አስረኛ ድርጅታዊ ጉባኤ በበርካታ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የመከረ ሲሆን ህዝባችንን እያማረረና እያንገላታ ያለው በአገልግሎት አሰጣጥ የሚታየው የመልካም አስተዳደር ችግር በአንገብጋቢነት ሊፈታ እንደሚገባው አቅጣጫ በማስቀመጥና ከፍተኛ አመራሩ ከማንም በላይ በኃላፊነት ወስዶ ሊሰራው የሚገባ ተቀዳሚ ተግባር ሊሆን እንደሚገባ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቀቀ፡፡
በጉባኤው የጉባኤ ሪፖርት ቀርቦ ጥልቅ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በኢህአዴግ መሪነት በልማት መስክ የተመዘገቡ ስኬቶች እንዳሉ ሆነው አገራችንን ከድህነት ለማላቀቅ የሚደረገው ትግል ከዚህ በፈጠነና በተሻለ ሁኔታ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገልጿል፡፡ የጉባኤ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የወስጠ ድርጅት ጥንካሬን በማጎልበት ኢህአዴግ በትጥቅ ትግሉ ያነበረውን የአይበገሬነትና የውስጠ ድርጅት ጥንካሬን በመድገም መንቃነቅ እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡   
የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የኢህአዴግ ሊቀመንበር በመሆን በድጋሚ የተመረጡት ጓድ ኃይለማርያም ደሳለኝ «ከዚህ ጉባኤ መልስ ፈጥነን ወደ ተግባር በመግባት ህዝባችን የሰጠንን አደራ ለመወጣት ከፍተኛ ርብርብ ማድረግ ይገባናል፡፡» ብለዋል፡፡ ለአባላት፣ ለመላው የአገራችን ህዝቦች፣ ለሰላማዊና ህጋዊ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች መልዕክት ያስተላለፉት ጓድ ኃይለማርያም በቀጣይ በሚኖሩ ስራዎች ሁሉም ከኢህአዴግ ጎን በመቆም የኢትየጵያን ህዳሴ ለማረጋገጥ መትጋት እንደሚገባው በአፅንኦት ገልፀዋል፡፡
ጓድ ኃይለማርያም ለመላው የአገራችን ህዝቦች ባስተላለፉት መልዕክትም ኢህአዴግና ኢህአዴግ የሚከተለው አቢዮታዊ ዴሞክራሲ መስመር የተመሰረተው በመላው የአገራችን ህዝቦች ሁለንተናዊ ተሳትፎ በመሆኑ ከድርጅቱ ጎን በመሰለፍ የጉባኤውን ውሳኔዎች በጋር እንዲፈፅሙ በጉባኤተኛው ስም ጥሪ ሲያስተላልፉ ተደምጠዋል፡፡ ለተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችም «በምርጫ 2007 ከኢህአዴግ ጋር በመፎካከር ህዝቡ የሰጠውን ብይን ተቀብላችሁ ያላችሁ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በፈቀዳችሁት ልክ ኢህአዴግ ከእናንተ ጋር ተባብሮ የጋር በሆኑና በሚያስማሙን ጉዳዮች ላይ አብሮ ለመስራት በሚያለያዩን ጉዳዮች ላይ ደግሞ ለመተጋገል የወሰነ በመሆኑ በዚህ አጋጣሚ መላው የአገራችን ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ለአገራችን ህዳሴ የበኩላችሁን እንድትወጡ በዚህ ጉባኤተኛ ስም ጥሪዬን አስተላልፋለሁ፡፡» ብለዋል፡፡
የኢህአዴግ ምክትል ሊቀመንበር በመሆን በድጋሚ የተመረጡት ጓድ ደመቀ መኮንን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አስረኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ የተካሄደው የመጀመሪያውን እድገትና ትራንስፎርሜሽን አጠቃልለን ወደ ሁለተኛው ምዕራፍ በምንገባበት ወቅት መሆኑ፣ በሁለተኛ ደረጃ አምስተኛው አገራዊ ምርጫ በድል ተጠናቆ ኢህአዴግ ሰፊ ይሁንታ አግኝቶ ከህዝብ አደራ የተቀበለበት ወቅት ላይ የተካሄደ ጉባኤ መሆኑን በማስታወስ ጉባኤው በነቃ ተሳትፎና በታሰበው መርሃ ግብር መሰረት መጠቃለሉን አረጋግጠዋል፡፡
በእያንዳንዱ ዘርፍ የተቀመጡ ጉዳዮች፣ በእያንዳንዱ ፕሮግራሞች የተቀመጡ ዝርዝር የአፈፃፀም አቅጣጫዎች ከቀጣይ እቅድ ጋር በተያያዘ ሁኔታ በውስጠ ድርጅትም የመንግስት ተቋማትን አቅም በመገንባትና የተጠያቂነት አሰራር በየደረጃው ተግባራዊ የሚሆንበትን ስርዓት እውን ለማድረግ መወሰኑንም ጓድ ደመቀ ገልፀዋል፡፡
ቀጣይ ጉባኤን ለማዘጋጀት የደቡብ ክልል የኢህአዴግን አርማ ከአዘጋጁ ድርጅት ህውሃት የተረከበ ሲሆን ጉባኤው የአጋር ድርጅቶችንና የተለያዩ አገራት ወዳጅ ፓርቲዎችን እውቅና በመስጠት ፍፃሜ አግኝቷል፡፡

ጉባኤ ጉባኤ

ኢህአዴግ የውስጠ ድርጅት ጥንካሬውን በማጎልበት የመልካም አስተዳደር ችግርን ለመቅረፍ የሚያስችለውን አቅጣጫ ተቀመጠ

ኢህአዴግ የውስጠ ድርጅት ጥንካሬውን በማጎልበት የመልካም አስተዳደር ችግርን ለመቅርፍ የሚያስችለውን አቅጣጫ ተቀመጠ «ህዝባዊ አደራን በላቀ እድገትና ትራንስፎርሜሽን» በሚል መሪ ቃል በመ‚ለ ከተማ ለአራት ቀናት በድምቀት ሲካሄድ የቆየው የኢህአዴግ አስረኛ ድርጅታዊ ጉባኤ በበርካታ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የመከረ ሲሆን ህዝባችንን እያማረረና እያንገላታ ያለው በአገልግሎት አሰጣጥ

ተጨማሪ ያንብቡ…

መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ቁርጠኛ አቋም የተያዘበት ጉባኤ

የኢህአዴግ መተዳደርያ ደንብ ድርጅቱ ከሁለት እስከ ሁለት ዓመት ተኩል ባለው ጊዜ ውስጥ ጉባኤውን እንደሚያካሂድ ይደነግጋል፡፡ በ1983 ዓም በትግራይ በቆላ ተንቤን በተባለ ስፍራ አንደኛ ድርጅታዊ ጉባኤውን አንድ ብሎ ማካሄድ የጀመረው ኢህአዴግ ሰሞኑን የተካሄደውን ጨምሮ አስር ስኬታማ ጉባኤዎችን አካሂዷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር/ኢህአዴግ/ 10ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ የአቋም መግለጫ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር/ኢህአዴግ/ 10ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ የአቋም መግለጫ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር/ኢህአዴግ /10ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ የተካሄደው አምስተኛው ጠቅላላ ምርጫ በማንኛውም መስፈርት ሲለካ እጅግ ዴሞክራሲያዊ፣ፍትሐዊ፣ግልጽ እና በመላው የሀገራችን ህዝቦች ዙሪያ መለስ ተሳትፎ የተፈፀመ ከመሆኑም በላይ የምልአተ ህዝቡን ንቁ ተሳትፎና ተአማኒነት ያተረፈ ሆኖ በተጠናቀቀበት ማግስት እንዲሁም

ተጨማሪ ያንብቡ…

ኢህአዴግ የመልካም አስተዳደር ችግርን ለመቅረፍ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ

ኢህአዴግ የመልካም አስተዳደር ችግርን ለመቅረፍ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ የኢህአዴግ 10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ዛሬ መልካም አስተዳደርን በተመለከተ ባደረገው ጥልቅ ውይይት ህዝቡ በየደረጃው የሚያነሳቸው የመልካም አስተዳደር ችግሮችን አመራሩ በቁርጠኝነት ለመፍታት የሚያስችለውን አቅጠጫ አስቀመጠ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ኢህአዴግ በአጋርነት ለመስራት የሚመርጡት በሳል ህዝባዊ ፓርቲ

ኢህአዴግ በአጋርነት ለመስራት የሚመርጡት በሳል ህዝባዊ ፓርቲ ‹‹ህዝባዊ አደራን በላቀ ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን›› በሚል መሪ ኃሳብ በመ‚ለ ከተማ እየተካሄደ ያለው የኢህአዴግ 10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ዛሬም እንደቀጠለ ነው፡፡ የጉባኤው ተሳታፊዎች ከትናንት ከሰዓት በኋላ ጀምረው በሰባት ቡድን ተከፋፍለው በኢህአዴግ ምክር ቤት ለጉባኤው በቀረበው ሪፖርት ላይ በመወያየት ላይ ናቸው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

10ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ ትናንት ነሓሴ 22ቀን 2007 ዓም በመቐለ ከተማ ሲጀመር የኢህአዴግ ሊቀመንበርና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ያደረጉት ንግግር

10ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ ትናንት ነሓሴ 22ቀን 2007 ዓም በመቐለ ከተማ ሲጀመር የኢህአዴግ ሊቀመንበርና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ያደረጉት ንግግር የተከበራችሁ ጉባኤተኞች፣ የተከበራችሁ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የመጣችሁ ተጋባዥ እንግዶች፣ የተከበራችሁ የውጭ እህት ፓርቲዎች የልኡካን አባላት ክቡራትና ክቡራን፣

ተጨማሪ ያንብቡ…

10ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ ‹‹ህዝባዊ አደራን በላቀ እድገትና ትራንስፎርሜሽን›› በሚል መሪ ቃል በመቀሌ ከተማ ተጀምሯል፡፡

ለትግሉ ሰማዓታት የህሊና ጸሎት በማድረግ የተከፈተው ጉባኤ የመክፈቻ ፕሮግራም በደማቅ ሁኔታ የቀጠለ ሲሆን የትግራይ ባህላዊ ጨዋታ አሸንዳን ጨምሮ በብሔርብሄረሰቦች ባህላዊ ጨዋታ ሞቅ ደመቅ ብሎ የተከፈተው ጉባኤ የኢህአዴግ አጋር ድርጅቶችና የተለያዩ አገር ወዳጅ ፓርቲ ተወካዮች የአጋርነትና የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ጉባኤው እንደደመቀ ቀጥሏል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…