ትኩስ ዜና

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርሞችን በጥልቀት በመገምገም ቀጣይ የኢኮኖሚ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ። የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ “በኢሕአዴግ ምክር ቤት ስብሰባዎች የመሳተፍ ዕድላችን መስፋት በክልላዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በጥልቀት እንድንወያይ አስችሎናል ” አጋር ፓርቲዎች የኢሕአዴግ ምክር ቤት ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታዎችን እና ያለፉትን ወራት የእቅድ አፈፃፀም በጥልቀት ገምግሞ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መደበኛ ስብሰባውን አጠናቀቀ። የኢህአዴግ ምክር ቤት ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ስብሰባውን ያካሂዳል፡፡ ከዛሬ አመት በፊት በኢህአዴግ ውስጥ የተጀመረው ለአብዮት የተቃረበ ሪፎርም በአገሪቱ የነበረውን የፖለቲካ መልክ መቀየር መቻሉን ድርጅቱ ገለጸ፡፡ ኦዲፒ ለአዳዲስ ድሎች እየተዘጋጀ መሆኑን የኦዲፒ ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ ገለጹ የኢትዮጵያና ጂቡቲ ህዝቦች ግንኙነትን ለማጠናከር የሁለቱ አገራት መሪ ፓርቲዎች አብረው እንደሚሰሩ ኢህአዴግ ገለጸ፡፡ ምክር ቤቱ የብሔራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፀደቋል፡፡ ምክር ቤቱ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን አባላትን ሹመት አፀደቀ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤት አባላቱ የተነሱ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ በቀጣይ ሊጉን የሚመሩ ወጣቶችን መረጠ የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ በአሁን ሰአት በውቢቷ ሀዋሳ ከተማ በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ 4ተኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ከጥር 19 ቀን ጀምሮ በሀዋሣ ከተማ ሊካሄድ ነው፡፡ የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታዎችን በዝርዝር ገምግሞ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መደበኛ ስብሰባውን አጠናቋል። ግዴታዬን እወጣለሁ፤ መብቴንም እጠይቃለሁ” በሚል መሪ ቃል ሃገራዊ የገቢ ንቅናቄ ተጀመረ፡፡ የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ በመቐለ ከተማ እያካሄደ ባለው የሊጉ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ጓዲት መሰረት መስቀሌን ከደኢህዴን በሊቀመንበርነት፣እንዲሁም ጓዲት መስከረም አበበን ከአዴፓ ምክትል ሊቀ መንበር አድርጎ መርጧል። የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ የአገሪቱን ሰላም በማስጠበቅ ሂደት ውስጥ ግንባር ቀደም ሆኖ ለመንቀሳቀስ መወሰኑ ተገለፀ በኢሕአዴግ ምክር ቤት ፅ/ቤት ምክትል ሃላፊ ጓድ መለስ አለሙ የሚመራው የድርጅታችን የልኡካን ቡድን የቻይና ጉብኝት እንደቀጠለ ነው የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በዛሬው እለት በደማቅ የመክፈቻ ስነስርአት በመቐለ ከተማ ተጀምሯል ።

ጉባኤ ጉባኤ

ፕሬዝዳት ሳህለወርቅ ዘውዴ ቃለ መሃላ ፈፅመው ኃላፈነታቸውን በትጋትና በታማኝነት አገርና ህዝብን ለማገልገል ቃል ገብተዋል፡፡

አምባሳደር ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ላለፉት አመስት ዓመታት በኃላፊነት ላይ የነበሩትን ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመን በመተካት አገሪቱን በፕሬዝዳንትነት የሚመሩ ይሆናል፡፡ አምባሳደር ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ የድፕሎማሲ ታሪክ ከአገር እስከ አለም አቀፍ ተቋማት ድረስ ኢትዮጵያን በመወከል ያገለገሉ አለም አቀፍ ዲፕሎማት ናቸው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

አምባሳደር ሳህለ ወርቅ ዘወዴ የኢፌዲሪ ፕሬዘዳንት ሆነው ተመረጡ

የሕዝብ ተወካዮችና የፌደሬሽን ም/ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው ስብሰባ አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴን የኢፌዲሪ ፕሬዘዳንት አድርጎ መርጧል፡፡ ተመራጭዋ ፕሬዚዳት አምሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ በሁለቱ ምክር ቤት ፊት ንግግር አድርገዋል፡፡ ፕሬዘዳት ሆነው በመመረጣቸው የተሰማቸውን ደስታ የገለጹ ሲሆን ለተሰናባቹ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ በሥልጣን ዘመናቸውን ለአገራቸው ላበረከቱት አስተዋጽዎ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ክቡር የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ላይ ያደረጉት ንግግር

አሮጌውን ዓመት ሸኝተን ወደ አዲሱ ዓመት በተሸጋገርንበት በዚህ በመስከረም ወር የመጨረሻ ሰኞ የኢፌዴሪ ሕገ-መንግስት በሚደነግገው መሠረት የሁለቱ ምክር ቤቶች የሥራ ዘመን መጀመርን በይፋ ለማብሰር በሚከናወነው የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝቼ ንግግር እንዳደርግ በመቻሌ ልባዊ ደስታ የተሰማኝ መሆኑን ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ 11ኛ መደበኛ ድርጅታዊ ጉባኤ የአቋም መግለጫ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ኢህአዴግ/ “ሀገራዊ አንድነት ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል 11ኛ መደበኛ ድርጅታዊ ጉባኤውን በብሄር ብሄረሰቦች መዲና፣ የህብረ ብሄራዊነትና የብዝሃነት መገለጫ እና የኢትዮጵያ ተምሳሌት በሆነችው ውቢቷ ሀዋሣ ከተማ ከመስከረም 23 – 25/2011 ዓ/ም ለሶስት ተከታታይ ቀናት አካሂዶ በስኬትና በድል አጠናቅቋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ምክር ቤቱ 10 ሴት የካቢኔ አባላት ጨምሮ በጥቅሉ 16 አዲስ የካቢኔ አባላትን ሹመት አፀደቀ፡፡

ምክር ቤቱ 10 ሴት የካቢኔ አባላት ጨምሮ በጥቅሉ 16 አዲስ የካቢኔ አባላትን ሹመት አፀደቀ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡ ጥያቄዎች ማብራሪያ በመስጠት ላይ ናቸው

ባነሰ ጊዜ የህዝብን ፍላጎት ማሟላት የሚቻለው የጋራ ዓላማ ያላቸውን ተቋማት በመሰብሰብ ነው ያሉት ዶር አብይ ለአንድ ዓላማ የሚሰሩ ተቋማት በአንድ መሰብሰባቸው የሰው ሃብትና አቅማቸውን አሰባስበው በመስራት የሚፈለገውን ውጤት ማስመዝገብ ይቻላል ብለዋል፡፡ አያይዘውም ተቋማት ተፈጥሯዊ የሆነ የእድገት ጉዞ ስላላቸው አካሄዳቸውን በየጊዜው ለውጥ በሚያስተናግድ መልኩ ማሻሻል ያስፈልጋቸዋል በማለት ተቋማቱ ዋናው ግባቸው የህዝብ ፍላጎትን ማሟላት ሊሆን እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

በታሪካዊ ምዕራፍ ውስጥ የተካሄደ ታሪካዊ ጉባዔ

ሰሞኑን የበርካቶች ቀልብ ሀዋሳ ላይ ነበር፡፡ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች፣ የፓርቲ አመራሮች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የውጭ ሀገራት ልዑካን ወዘተ ሀዋሳ ላይ ከትመዋል፡፡ በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት የመገናኛ ብዙኃንም የብዝኃነት ተምሳሌት በሆነው በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ዋና ከተማ ሀዋሳ ቀድመው ተገኝተዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ቪዲዮ ቪዲዮ

Visitor counter Visitor counter

Today       

1465

       የዛሬ ጎብኚ

Yesterday       

1381

       የትናንት ጎብኚ

This Month       

55786

       የዚህ ወር ጎብኚ

This Year       

296222

       የዚህ ዓመት ጎብኚ

Total        

407017

       አጠቃላይ ጎብኚ