ትኩስ ዜና

የብልጽግና ፓርቲ የዕውቅና ምስክር ወረቀት እንዲሰጠው ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥያቄ አቀረበ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህምድ የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊነት ዓለም አቀፉ ሕብረተሰብ ኢትዮጵያ ላይ ያለውንም ተስፋ ያመላከተ መሆኑን ተናገሩ፡፡ የውህደቱ ዓላማና አስፈላጊነት ኢህአዴግን አጋር ድርጅቶቹን በማካተት ህብረ ብሔራዊ ፓርቲ ለማድረግ የተካሄደው ዝግጅት መጠናቀቁን የኢህአዴግ ምክር ቤት አስታወቀ። የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ውይይትና ድርድርን የተመለከተ ውይይት ተካሄደ ኢህአዴግና ሀገር አቀፍ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይት፣ ክርክርና፣ ድርድር ለማድረግ በሚያስችላቸው ደንብ ረቂቅ ላይ ቀጣይ ውይይታቸውን ዛሬ አደረጉ፡፡ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ጀመረ “በሀገራችን የተገነባው ዴሞክራሲዊ አንድነት የእግር እሳት የሆነባቸው የጥፋት ኃይሎች ሴራ መታግል ይባል ” ጓድ ሽፈራው ሽጉጤ የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት ኃላፊ ኢህአዴግ እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ውይይትና ድርድር ለማካሄድ ተስማሙ የወጣቱን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የወጣት አደረጃጀቶችን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ በኪራይ ሰብሰቢነት ላይ በሚደረገው ትግል ወጣቶች ግንባር ቀደም ሚና መጫወት እንደሚገባቸው ተገለጸ በህዳሴው ጉዞ ላይ የሚያጋጥሙ መደነቃቀፎች ሴቶችን ይበልጥ ተጎጂ የሚያደርጉ በመሆናቸው በንቃት ሊታገልዋቸው እንደሚገባ ተገለጸ በዓሉ የህዝቦችን እኩልነት፣ አብሮ የመኖር እና የመቻቻል እሴቶች ለማጎልበት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተገለጸ የኦሮሞ ህዝብ የገዳ ስርዓት በዩኔስኮ በማይዳሰሱ የሰው ልጅ ወካይ ቅርስነት ተመዝግቧል የቻይና ምክትል ፕሬዚዳንት ሊ ዩዋንቻኦ በኢትዮጵያ ይፋዊ ስራ ጎብኝት እያካሄዱ ነው፡፡ 11ኛውን የብሄሮ ብሄረ ሰቦችና ህዝቦች በዓል ለማክበር ዝግጅት ተጠናቋል አዲስ የሚዋቀረው የፌዴራል መንግስት ካቢኔ በዛሬው እለት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይቀርባል እድገቱ የወለዳቸውንም ሆነ በአፈፃፀም ችግር ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በተከተለ አግባብ እንደሚፈቱ ተገለፀ፡፡ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የህዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ በንግግር ከፍቱ የገዳ ስርዓት የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የላቀ ፋይዳ እንዳለው ተገለጸ

ኢህአዴግ

ኢህአዴግ አገር የመምራት ሃላፊነትን ከተረከበ ጊዜ ጀምሮ ከውስጥም ከውጭም የሚነሱ በርካታ ውጣ ውረዶችን ያስተናገደ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጣጣምና የህዝባችንን ሁለንተናዊ መለወጥ ታሳቢ ያደረገ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ስርዓት በማራመድ በውጭ ሃይል ተፅእኖ የሚጠመዘዝ ድርጅት አለመሆኑን ገና በጠዋቱ በተግባር ያሳየ ድርጅት ነው፡፡

ከደርግ ውድቀት ማግስት አገራችን የመበታተን ስጋት ውስጥ የነበረችበት ሁኔታ ቢኖርም መላ የሃገሪቱን ህዝቦች በማስተባበርና በብስለት በመምራት ዴሞክራሲያዊ አንድነቷ በፅኑ መሰረት ላይ እየተገነባ እንዲዘልቅ አስችሏል። ህገ መንግስታችን የአንድነታችንና የመከባበራችን ማሰሪያ ውል እንዲሆን በሚያስችል መልኩ በህዝብ ሙሉ ተሳትፎ ተቀርፆ በመፅደቁ ያንን የመበታተን ስጋት ተሻግረን በጋራ ለዘላቂ ለውጥ መረባረብ ጀምረናል።

የብልጽግና ፓርቲ የዕውቅና ምስክር ወረቀት እንዲሰጠው ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥያቄ አቀረበ

  በቅርቡ ውህደት የፈጸሙት የኢህአዴግ እህትና አጋር ፓርቲዎች በኢትዮጵያ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ...

ተጨማሪ ያንብቡ…

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህምድ የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊነት ዓለም አቀፉ ሕብረተሰብ ኢትዮጵያ ላይ ያለውንም ተስፋ ያመላከተ መሆኑን ተናገሩ፡፡

ፕሬዚዳንቷ ማምሻቸውን በጠቅላይ ሚኒስተሩ የኖቤል የሰላም ሽልማት የእንኳን ደስ አላችሁ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በዚህ መግለጫቸው ሀገር ውስጥ ላሉ እና በውጭ ሀገራት ለሚገኙ መላው ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንኳን ደስ አላችሁ መልክት አስተላፈዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ የ2019 የኖቤል የሠላም ሽልማትን በማሸነፍ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ሆነዋል ነው ያሉት፡፡ ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ ጀምሮ ሰላም፣ ይቅርታና ፍቅርን ከማቀንቀን አቋርጠው እንደማያውቁም አንስተዋል፡፡ በሀገር ውስጥ የነበረውን አስፈሪ የፖለቲካ ፍጥጫ በማርገብ፣ በውጭ ሀገር የነበሩ የፖለቲካ ድርጅቶች ወደ ሀገር እንዲገቡ በማድረግ፣ ያለፈውን ታሪክ ዕሴቶች አስጠብቀን እንድንጓዝ ማድረጋቸውንም አንስተዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የውህደቱ ዓላማና አስፈላጊነት

ስለ አዲሱ ውህድ ፓርቲ በተሻለ ለመገንዝብ ይረዳ ዘንድ አላማውና አስፈላጊነቱ እንደሚከተለው በስፋት ተተንትኖ ቀርቧል፡፡ የሳምንት መወያያ ርዕስ ላይም ስለ ውህደቱ ላነሳችው ስጋትና ጥያቄዎች በተወሰነ መልስ ይሆናችሁል፡፡ በተከታታይነትም ግልጽነት የመፍጠር ስራ ይቀጥላል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

Back

አሰራሮቻችንን በማዘመን የወጣቱን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንረባረብ

"ከኤፊ ሰውነት"
በአገራችን በተለይ ካሳለፍነው ዓመት ጀምሮ በወጣቱ በኩል በተደጋጋሚ ሲነሱ የምንሰማቸው ጥያቄዎች በዋናነት ከተጠቃሚነት ጋር የተያያዙ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ ከጫፍ እስከ ጫፍ በሚባል ሁኔታ የወጣቱ መሰረታዊ ጥያቄ የስራ እድል ፈጠራ ጉዳይ እንደሆነም እንገነዘባለን፡፡
ውድ አንባብያን በተደጋጋሚ እንደሚገለፀውና ነባራዊ ሁኔታውም እንደሚያስገነዝበው በአገራችን አሟጠን ያልተጠቀምንበትና የእድገታችንም መስረት የሆነው የውስጥ አቅማችን የሰው ጉልበትና መሬት ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት ኢህአዴግ አገር የማስተዳደር ህዝባዊ አደራ  በተረከበበት ማግስት የወሰደው እርምጃም ይህን የውስጥ አቅማችንን መጠቀም የሚያስችለንን ከህገ መንግስት ጀምሮ የተለያዩ ፖሊሲና ስትራቴጂዎችን መቅረፅ ነበር፡፡ ከዚህ አኳያ በተለይ ከፍተኛ ቁጥር የሚሸፍነው የአገራችን ህዝብ በሚኖርበት አካበቢ ድህነት ተኮር የሆነ የገጠር ልማት ፖሊሲን በመተግበር የአርሶ አደሩን ጉልበትና መሬት ማዕከል ያደረገ የልማት ስትራቴጂ ተነድፎ ተግባራዊ በመደረጉ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የአርሶ አደሩ ህይወት በቀጣይነት ከመለወጡ ባሻገር ዓለም አቀፍ አድናቆት የተቸረው ኢኮኖሚያዊ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል፡፡
በተመሳሳይ ደረጃ በከተማ ያለውን ሰፊ ጉልበትና ውሱን ካፒታል ያቀናጀና የከተማ ህዝብ ኑሮ የሚያሻሽል ብሎም አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታውን የሚቀይር የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ስትራቴጂ ተንድፎ ተግባራዊ ከተደረገ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት በውሱን ካፒታል ሰፊ የስራ እድል መፍጠር የሚችሉ ከመሆናቸው ባሻገር በሁሉም ከተሞች ከዚያም አልፎ በገጠሮች ሊደራጁ የሚችሉ መሆናቸው ስትራቴጂው በተሟላ መልኩ በተተገበረ ቁጥር አመርቂ ውጤት ለማምጣት ሰፊ እድል የሚሰጥ መሆኑ አያጠያይቅም፤ በተግባር የተረጋገጠውም ይህ ነው፡፡
ይሁንና ዘርፉ በተለይ የኢኮኖሚ ልማት አንዱ ማጠንጠኛ የሆነውን ሰፊ የስራ እድል የመፍጠር ራዕይ የሚያሳካ ሆኖ ሳለ አሁንም በበርካታ መሰናክሎች ተከቦ ዛሬም የወጣቱን ጥያቄ በተሟላ መልኩ የመመለስ ዓቅሙ በየጊዜው ፈተና ውስጥ ሲገባ እንታዘባለን፡፡ ዘርፉ  ሚሊዮኖችን አሰልፎ የሚሊዮኖችን ህይወት ከመቀየር ባሻገር ለተያያዝነው የህዳሴ ጉዞም የማይተካ ሚና መጫወት የሚችል የዕድገታችን ሞተር መሆን የሚያስችል ቁመና መፍጠር ሲገባው አሁንም በተደራራቢ ተግዳሮቶች እየተተበተበ መጥቶ የወጣቱን ተስፋ እስከ መፈታተን ደርሷል፡፡
ውድ አንባብያን እዚህ ላይ መዘንጋት የሌለበት እውነታ ቢኖር ኢህአዴግ የሚመራው ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መንግስት የዘርፉን ልማት የሚያሳልጡና ዘርፉን ለመደገፍ በተግባር ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በሚመልስ መልኩ በ1994፣ 1999 እና በኋላም በ2003 የተቀረፁት ስትራቴጂዎች ጥንካሬ ነው፡፡ ኢህአዴግና እና በኢህአዴግ የሚመራው ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መንግስታችን ለወጣቶች የስራ ዕድል በመፍጠር ወጣቶቻችን በልማቱ ላይ ንቁ ተሳታፊን ከልማቱም ፍትሐዊ ተቋዳሽ እንዲሆኑ በየጊዜው አቅጣጫ ያስቀምጣሉ፤ ለተፈፃሚነቱም ቀን ተሌሊት ይተጋሉና!  
የጥቃቅንና አነስተኛ ስትራቴጂ የዘርፉ ዋነኛ ችግር የካፒታል እጥረት በመሆኑ የካፒታል እጥረቱን ለመፍታት የአበዳሪ ተቋማትን አቅም በማጎልበት ተከታታይነት ያለው ድጋፍ መስጠት እንደሚገባ ያመላክታል፡፡ የካፒታል እጥረታቸውን መቅረፍ ብቻ ወደ ዘርፉ የሚገባውን ስራ ፈላጊ ቁጥር እንደማይጨምር በግልፅ ያስቀመጠው ስትራቴጂው የመስሪያ ቦታዎችን ሰርቶ በማቅረብ ጭምር በዘርፉ የሚገጥመውን ተግዳሮት መፍታት እንደሚገባም ስትራቴጂው በግልፅ ያስቀምጣል፡፡   
አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማትን ለማደራጀት የሚያስፈልገው ካፒታል ያን ያህል ከባድ አይደለም፡፡ ዋናው ጉዳይ በተግባር ላይ ለመሰማራት ቆርጦ መነሳት፣ የተወሰነ ስራ ለመስራት የሚያስችል ክህሎት መጨበጥ ብቻ ነው፡፡ በእኔ እሳቤ ይህን አደራጅቶ በተሟላ መልኩ መተግበር ደግሞ በዋናነት ዘርፉን የሚመራ አካል ድርሻ ነው፡፡ አሁን ያለው ነባራዊ አፈፃፀም ሁኔታ የሚያሳየው ግን ከዚህ በተቃራኒ ነው፡፡ አሁንም የስራ እድል ፈጠራ ጉዳይ አንገብጋቢና የበርካታ ወጣቶች ጥያቄ እንደሆነ ቀጥሏል፡፡
ወጣቶች ከመደራጀት ጀምሮ በተለያዩ እርከኖች የሚያልፉባቸው መንገዶች ሁሉ ውስብስበ እየሆኑና አሰራሩም ለኪራይ ሰብሳቢነት የተጋለጠ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ዘርፉ ፈቀቅ ብሎ የወጣቶችን ጥያቄ ስር ነቀል በሆነ መልኩ መፍታት እንዳይችል አድርጎታል፡፡ በዚህም በዘርፉ እስካሁን የተከናወኑ ወርቃማ ስራዎች በአግባቡ እንዳይታዩና አጠቃላይ ድባቡ ጠቆርቆር ብሎ እንዲታይ አድርጓል፡፡ አሁን ያለው አዝጋሚ ጉዞ በአግባቡ ካልተቀየረ ደግሞ ውስብስብ ወደሆነ ችግር ውስጥ መገባቱ አይቀሬ ነው የሚል የግል እይታ አለኝ፡፡
የስራ እድል ፈጠራን በተመለከተ ስናወራ በዋናነት የምናነሳው በታችኛው የመንግስት አስፈፃሚ አካላት አካበቢ ያሉ የአፈፃፀም ጉድለቶች ናቸው፡፡ በወረዳና ክፍለ ከተማ ደረጃ በእጅ ላይ ያሉ ሃብቶችን በተገቢውና ለሚገባው አካል ከማዋል ረገድ ተግዳሮቶች እንደሚስተዋሉ ወጣቶች ያነሳሉ፡፡ ስራዎችን አውቆ የሚደራጀውን አካል በዛ መንፈስ ከማደራጀትና የስልጠናም ሆነ የብድር ብሎም የመስሪያና የመሸጫ ቦታ አቅርቦቱን በተደራጀ አኳኋን ለይቶ ከማቅረብ አኳያ ክፈተት አለ፡፡ እንደውም አንድ ወዳጄ ሲያወራ የሰማሁትን ላካፍላችሁ፣ ለመደራጀት፣ ፍቃድ ለማውጣት የሚወስደው ጊዜና ምልልስ፤ ቦታና ብድር ለመስጠት የሚወስደውን ጊዜ በማሰብ ሃሞትህ ስለሚፈስ ተሯሩጦ መስራት ይሻላል በሚል መንፈስ ለጊዜህ አስበህ ሂደቱን ሳትጨርስ ታቆማለህ ያለኝን አስታውሳለሁ፡፡ ይህ የሚያሳየው ዘርፉ ላይ ያለው አጠቃላይ የቢሮክራሲ አሰራር የወጣቱን ፍላጎት ታሳቢ ባደረገ መልኩ መታረም እና መሻሻል እንዳለበት ነው፡፡ በእርግጥ አዲሱ የኢትዮጵያ ወጣቶች የልማትና የዕድገት ፓኬጅ እና የወጣቶች የልማትና የዕድገት ስትራቴጂ ሰነዶች እነዚህ አሰራሮችን ለማረም በማሰብ ጭምር የተዘጋጁ ናቸው፡፡
ይህ ሁኔታ ፈፅሞ መቀየር የሚገባው ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡ ከያዝነው ዓመት ነባራዊ ሁኔታ እንኳን ተነስተን ብንነጋገር የወጣቶችን ጥያቄ በተደራጀ መልኩ ለመፍታት እንዲቻል የስራ አጥ ምዝገባ ተካሂዶ እንደነበረ እናስታውሳለን፡፡ በምዝገባ ሂደቱ ላይ በርካታ ወጣቶች ይህ ሁኔታ በተደጋጋሚ መካሄዱን በመግለፅ አፈፃፀሙ ላይ ጥርጣሬያቸውን አንፀባርቀዋል፡፡ ይህ ጥርጣሬ ጤናማ ነው የሚል መነሻ አለኝ፡፡ ከዚህ በፊት በተመዘገበው ልክ ሁሉም ላይ ርብርብ ባለመደረጉና ጥቂቶች ብቻ በሂደቱ ተጠቃሚ ሆነው በማለፋቸው የመጣ ሳይሆን አይቀርም፡፡ እውነት እንነጋገር ከተባለ ደግሞ ችግሩ አሁንም መሬት ላይ በመሆኑ ኢህአዴግ በገባው ቃል መሰረት ችግሩን ለመፍታት የሚያደርገው ጥረት ተስፋ ሰጪና በእርግጥም ለችግሩ ተሰጠው ክብደት በማየት ቀጣዩ ጉዞ ብሩህ እንደሆነ በግልፅ አመላካች ቢሆንም ወጣቶቹ የእስካሁን አፈፃፀም እያዩ አሁንም ከስጋት ነፃ እንዳይሆኑ አድርጓቸዋል፡፡  
በእርግጥ አሁን የስራ አጥ ከመለየት ባለፈ በየስልጠና ማዕከሎች የማስገባትና እንደ አገር ደግሞ በምን ዘርፎች ላይ ቢሰማሩ ውጤታማ ይሆናሉ በሚል የመለየት ስራ በተሻለ ሁኔታ ተሰርቷል፡፡ ይህ በራሱ የሚበረታታ እርምጃ ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡ ከወጣቱ ፍላጎትና ጉጉት አኳያ ብናየው ደግሞ ሂደቱ መፍጠን እንዳለበት ይሰማኛል፡፡
ወጣቱ ባለፉት ዓመታት ያነሳ የነበራቸው የተጠቃሚነት ጥያቄዎች አግባብነታቸው የሚያጠያይቅ አይደለም በእኔ እይታ፡፡ ይህ ጥየቄ ትክክል መሆኑን በመገንዘብ መንግስት እየወሰደ ያለው ርምጃም ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡ የ10 ቢሊዮን ብር የተዘዋዋሪ ፈንድ ጥቅም ላይ ማዋል አንዱ ወርቃማ እርምጃ ነው፡፡ በያዝነው ዓመት 5 ቢሊዮን ብር ጥቅም ላይ እንደሚውል ተገልጿል፡፡ ይህ ተዘዋዋሪ ፈንድ በብድር መልክ የሚሰጥ ቢሆንም ከወለድ ነፃ በሆነ መልኩ ለተጠቃሚ ወጣቶች የሚተላለፍ ሆኖ ወጣቶቹ አትራፊ ከሆኑ በኋላ ተመላሽ በማድረግ ወደሌሎች ዕድሉ ያላገኙ ወጣቶች እየተዘዋወረ በርካታ ወጣቶችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡ በመሆኑም ይህን ጉዳይ የሚያስፈፅሙ የዘርፉ ባለሙያዎች ፍፁም ቁርጠኛ በሆነ መንፈስ ተግባራዊ ሊያደርጉት ይገባል ባይ ነኝ፡፡
በዘርፉ ሊያሰራ የሚችል ስትራቴጂና መዋቅር አለ፡፡ ይህን ተግባራዊ የሚያደርጉ በየደረጃው ያሉ አካላት ፍፁም አገልጋይ በሆነ ስሜት ውስጥ ሆነው የዘርፉን አገራዊ ጥቅም ጭምር በማጤን ለውጤታማነቱ ሉረባረቡ ይገባል፡፡ ለመደራጀት፣ ለስልጠና፣ ብድር ለመውሰድም ሆነ የመስሪያና መሸጫ ቦታ ለማግኘት የሚባክን  አላግባብ የሆነ ጊዜ ፈፅሞ መቅረት ይኖርበታል፡፡  ይህን ማድረግ ሲቻል በአንቀሳቃሹ በኩል ያሉ ተግዳሮቶችንም በግልፅ ለመለየት እድል ይሰጣል፡፡ በመሆኑም የዘርፉ እንቅስቃሴ አሁን ካለበት ዘገምተኛ አካሄድ ወጥቶ የወጣቱን ፍላጎት ማርካት ወደመቻል መሸጋገር ይኖርበታል፡፡ በጊዜ የለንም መንፈስ በመስራት በእጃችን ያለውን ሃብት መጠቀምና ዘርፉና የዘርፉ አንቀሳቃሾች ሊያበረክቱ የሚችሉትን አገራዊ ኢኮኖሚያዊ አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት ለተፈፃሚነቱ ሁሉም በጋራ መትጋት ይገባዋል፡፡ ሰላም፡፡


Visitorcounter Visitorcounter

Today       

1901

       የዛሬ ጎብኚ

Yesterday       

1604

       የትናንት ጎብኚ

This Month       

26038

       የዚህ ወር ጎብኚ

This Year       

232161

       የዚህ ዓመት ጎብኚ

Total        

428350

       አጠቃላይ ጎብኚ