Skip to Content
   አማርኛ    እንግሊዘኛ    ያግኙን    ሴትች ሊግ    ወጣት ሊግ

ኢህአዴግ

ኢህአዴግ አገር የመምራት ሃላፊነትን ከተረከበ ጊዜ ጀምሮ ከውስጥም ከውጭም የሚነሱ በርካታ ውጣ ውረዶችን ያስተናገደ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጣጣምና የህዝባችንን ሁለንተናዊ መለወጥ ታሳቢ ያደረገ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ስርዓት በማራመድ በውጭ ሃይል ተፅእኖ የሚጠመዘዝ ድርጅት አለመሆኑን ገና በጠዋቱ በተግባር ያሳየ ድርጅት ነው፡፡

ከደርግ ውድቀት ማግስት አገራችን የመበታተን ስጋት ውስጥ የነበረችበት ሁኔታ ቢኖርም መላ የሃገሪቱን ህዝቦች በማስተባበርና በብስለት በመምራት ዴሞክራሲያዊ አንድነቷ በፅኑ መሰረት ላይ እየተገነባ እንዲዘልቅ አስችሏል። ህገ መንግስታችን የአንድነታችንና የመከባበራችን ማሰሪያ ውል እንዲሆን በሚያስችል መልኩ በህዝብ ሙሉ ተሳትፎ ተቀርፆ በመፅደቁ ያንን የመበታተን ስጋት ተሻግረን በጋራ ለዘላቂ ለውጥ መረባረብ ጀምረናል።

እባክዎን ማንኛውም አስተያየት ካልዎት ክልክ በማድረግ ይፃፉ!

ስለአስተያየትዎ እናመሰግናለን!!!

ዜና ዜና

Back

አስራ አምስት ተደራዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ስርዓቱ ቅይጥ ትይዩ እንዲሆን ተስማሙ።

ኢህአዴግን ጨምሮ 16 አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ህግ 532/99 በሚመለከት አምስተኛ ድርድራቸውን ዛሬ አካሄደዋል።

በድርድሩ አስራ አራት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገዢው ፓርቲ ያቀረበው የአብላጫና ተመጣጣኝ የምርጫ ስርዓት /ቅይጥ ትይዩ/ በምርጫ ህጉ ይካተት የሚለውን ሃሳብ ተቀብለዋል።

የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ) በበኩሉ የምርጫ ህጉ ሙሉ ተመጣጣኝ እንዲሆንና ይህ መሆን ካልቻለ ደግሞ የነበረው የአብላጫ ድምፅ ስርዓት እንዲቀጥል አቋም ይዟል።

ይሁን እንጂ በቅይጥ ትይዩ የምርጫ ስርዓት የተስማሙ ፓርቲዎች የአብላጫና ተመጣጣኝ ድምፅ የመቶኛ ድርሻ ምን ያህል ይሁን በሚለው ምጣኔ ላይ የተለያዩ አቋሞችን አንጸባርቀዋል።

ገዢው ፓርቲ "85 በመቶ የአብላጫ ድምፅ እና 15 በመቶ የተመጣጣኝ ድምፅ ያጣመረ የቅይጥ ትይዩ የምርጫ ስርዓት ይሁን" የሚል አቋም መያዙን የፓርቲው ተደራዳሪ አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ ገልፀዋል።

በገዢው ፓርቲ የቀረበው ይህ አቋም ከመላው ኦሮሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (መኦህዴፓ) ድጋፍ አግኝቷል።

በጋራ ተጣምረው የሚደራደሩት አስራ አንዱ ፓርቲዎች ደግሞ ከዚህ በፊት ያቀረቡትን የሃምሳ ሃምሳ በመቶ የአብላጫና ተመጣጣኝ ምርጫ ድምፅ ድርሻን በማሻሻል፤ 60 በመቶ የአብላጫ እና 40 በመቶ ተመጣጣኝ እንዲሆን ከፓርቲዎቹ ተወካይ ተናጋሪዎች መካከል አቶ ትዕግስቱ አወሉ ገልፀዋል።

የገዳ ስርዓት አራማጅ ፓርቲ በቅይጥ ትይዩ የምርጫ ስርዓት ውስጥ የአብላጫና ተመጣጣኝ ድምፅ "የመቶኛ ድርሻ ምን ያህል ይሁን" በማለት አስራ አንዱ ፓርቲዎች ያቀረቡትን ሃሳብ ደግፏል።

የመላው ኢትዮጵያውያን ብሔራዊ ንቅናቄ (መኢብን) ቅይጥ ትይዩ የምርጫ ስርዓቱ 75 በመቶ የአብላጫ እና 25 በመቶ ተመጣጣኝ እንዲሆን ተደራድሯል።

ከኢራፓ ውጪ አስራ አምስቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተመጣጣኝ የምርጫ ስርዓት የመቶኛ ድርሻ ተመሳሳይ አቋም ባይዙም፤ ይህን የምርጫ ስርዓት የሚያሟሉ አዳዲስ የፓርላማ ወንበሮች እንዲጨመሩ ተስማምተዋል።

በዚህ መሰረት የፓርላማ አባላት ቁጥር ከፍ እንደሚል ይጠበቃል።

በተያያዘ ዜና የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ) በምርጫ አብላጫ ድምጽ አግኝቶ አገሪቷን እያስተዳደረ ያለውን ፓርቲ "ከስልጣን ይውረድ" የሚል ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠቱ ከገዢው ፓርቲ ቅሬታ ቀርቦበታል።

መግለጫው ህገመንግስቱን እንደሚጻረር የገለፀው ገዢው ፓርቲ፤ "ኢራፓ ኢ-ህጋዊ አካሄዶችን እየተጠቀመ በመሆኑ ከእርሱ ጋር ለመደራደር እቸገራለሁ" ሲል ቅሬታውን ገልጿል።

ኢህአዴግ ቅሬታ የቀረበበት ፓርቲ በቀጣዩ የድርድር ቀን በጉዳዩ ዝርዝር ማብራሪያ ይዞ እንዲቀርብ የጠየቀ ሲሆን፤ ኢራፓ በበኩሉ ለቀረበበት ቅሬታ መልስ ይዞ እንደሚቀርብ ተናግሯል።

ፓርቲዎቹ በቅይጥ የምርጫ ስርዓት ውስጥ የአብላጫ እና የተመጣጣኝ ድምጽ የመቶኛ ድርሻ ምን ያህል ይሁን በሚለው ሃሳብ ላይ ለመደራደር ለጥቅምት 17 ቀን 2010 ዓ.ም ቀጠሮ መያዛቸው ኢዜአ ዘግቧል፡፡

 

 


መጣጥፎች መጣጥፎች

የዕውቀት ተቋማት የግጭት ማዕከል ለማድረግ መንቀሳቀስ ከወንጀል የባሰ ወንጀል

ትምህርት የአንዲት ሀገር ቁልፍ የዕድገት መሳርያ ነው፡፡ ያለ ትምህርት ዕድገት የበለጸገ ሃገር የለም፡፡ አሁን ዓለማችን የደረሰችበት የዕድገትና የስልጣኔ ደረጃ ያለ ትምህርት ከቶም አይታሰብም፡፡ የትምህርት አሻራ በስነ ህንጻ፣ በጤና፣ በምርምር፣ በከተማ ልማት በጠቃላይ በሁለንናዊ የህይወት መስክ በጉልህ ይታይል፡፡ ለዚህም ነው ሃገሮች ለትምህርት ልዩ ትኩረት ሰጥተውና ከፍተኛ በጀት መድበው የሚንቀሳቀሱት፡፡ በሀገራችን ዘመናዊ ትምህርት ከተጀመረ ረጅም ዘመናትን ተሻግሯል፡፡ ዕደገቱ ግን አዝጋሚ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ መስኩ ፈጣን ለውጥ አስመዝግቧል፡፡ በአራቱም አቅጣጫዎች ትምህት ቤቶች በብዛት ተገንብተዋል፡፡ የከፍተኛ ተቋማት ተማሪዎች ቁጥር ከፍተኛ ዕድገት በማሳየት ይገኛል፡፡

ሀገራዊ እሴቶቻችንን ለሀገራዊ ለውጥ እንጠቀምባቸው!

አገር በእናት ትመሰላለች፡፡ እናት አገሬ! እምዬ ኢትዮጵያ! እና መሰል ንግግሮችን ብዙዎቻችን ለአገራችን ያለን ዋጋ ከፍ ያለ መሆኑን ለመግለጽ እንጠቀምበታለን፡፡ በእርግጥም አገር እንደ እናት ናት፡፡ አንዱን ትልቅ ሌላውን ትንሽ አድርጋ አታይም፡፡ አገር እንደ እናት ናት በልጆቿ መሃል አድሎ አትፈፅምም፡፡ አገር እንደ እናት ናት ጓዳዋ ለሁሉም እኩል ነው፡፡ አገር እንደ እናት ናት ፍቅሯ በፆታ፣ በእድሜ አይገደብም፡፡ የእናት ሆድ ዥንጉርጉር ነው እንዲሉ በመልክም በባህሪም የሚለያዩ ልጇቿን እንደየባህሪያቸው አቻችላ ለታረዘው ልብስ፣ ለራበው ምግቡን፤ ለጠማው ደግሞ ውሃ በእናትነት በረከቷ ስለምትለግስ በእርግጥም አገር እንደ እናት ናት፡፡

የፍትህ ተቋማት ለሀገራዊ ዕድገት

እንደ ሀገር ባለፈው አንድ ዓመት በተካሄደው ሀገራዊ ለውጥ የመዋቅር ሂደቱን እንደገና በመፈተሸ ለህዝብ በሚመች መልኩ ከተደራጁ የመንግስት ተቋማት መካከል አንዱ የፍትህ ተቋም ነው፡፡ ህዝቡ በፍትህ ተቋማት ላይ አመኔታ በእጅጉ ይጨምር ዘንድ አሰራራቸውን በማዘመን ፈጣን ቀልጣፋና ሀላፊነት በተሞላበት መንገድ ሊሰሩ ይገባል፡፡ የልማት ስራዎችን ማረጋገጥ ለፍትህና መልካም አስተዳደር መረጋገጥ የበኩሉን አዎንታዊ ሚና እንዳለው ሁሉ ፍትህንና መልካም አስተዳደርን እያረጋገጡ መሄድም ለልማቱ መፋጠን ቀላል የማይባል አዎንታዊ ድርሻ ይኖረዋል። የፖለቲካ ምህዳሩ በሰፋበት ፣ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማምጣት የተለያዩ እርምጃዎችን በመስወድ የመንግስት ቁርጠኝነት በታየበት፣ የማህበራዊና አካባቢያዊ እንቅስቃሴ ምሰሶ በሆነችው ኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተመዘገበ ያለው የኢኮኖሚ እድገት የሚያበረታታ ነው።

እንደገና ወደ ኋላ ለማን በጀ?

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች ላይ የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት የክልሉን ልማት ወደ ኋላ ለመመለስ ብቻ ሳይሆን ለዘመናት በመተሳሰብና በመቻቻል አብሮ ከኖረው ከወንድሙ የኦሮሞ ህዝብ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማሻከርና እርስ በእርስ የጥርጣሬ መንፈስ እንዲፈጠር በማድረግ የመተባበርና የመደጋገፍ አቅሙን ለማዳከም ታልሞ የተሰራ ሴራ ነው፡፡ በአራቱም የሀገሪቱ ማዕዘናት የተጀማመሩና የኢኮኖሚ ምህዋሩን አንድ ደረጃ ማሳደግ የሚያስችሉ ልማቶችን ከመደገፍና ደጀን ከመሆን ይልቅ ኢ-ምክንያታዊ በሆኑ ነገሮች ሰበቦችን በመፍጠር ብሔርን መሰረት አድርገው ሁከትና አለመረጋጋት እንዲፈጠር በማድረግ አንዳንድ አፍራሽ ኃይሎች መንግስትን የማዳከም ስራ ላይ ተጠመደዋል፡፡ የሰው ህይወት እንዲጠፋ፣ የህዝብና መንግስት ንብረቶችን ማውደም፣ እንዲሁም ይህንኑ ግርግር መነሻ በማድረግ በዝርፊያና ስርቆት ወንጀሎች ላይ በመሰማራት በህገ ወጥ መንገድ የግል ሀብታቸውን ለማፍራት የሚኳትኑ ጥቂት እፉኝቶች የሌት ተቀን ስራቸው አድርገውታል፡፡

ለሚወረወርልን እሳት ጭድ እየመገብነው ነው ወይስ ውሃ እየቸለስንበት?

በዚህ ይህ የኔ አካባቢ ነው፣ አንተ መጤ ነህ፣ ውጣልኝ/ውጭልኝ እስከ መባባል ተደርሶ፤ የሰው ህይወት እየጠፋና በርካቶች ለዘመናት ከኖሩበት የትውልድ ቀዬአቸው እየተፈናቀሉ ነው፡፡ ይህ ግጭት እውነትም በህዝቦች መካከል እየተፈጠረ ያለ ግጭት ነው ወይ? ሲባል ሁሉም አፉን ሞልቶ በጭራሽ፤ እንዴት ተደርጎ፤ በተድላ ጊዜ በደቦ አመርተን ለአገር የምንተርፍ፣ በችግራችን ጊዜ ደግሞ አንድ ቂጣ ተካፍለን በልተን አድረን ክፉ ደጉን አብረን ያሳለፍን፤ አንድ እናት ገቢያ ስትሄድ የአንዷን እናት ጡት ለሁለት ጠብተን ያደግን ሰዎች ምን ቆርጦን ጦር እንማዘዛለን? እንላለን፡፡ ከግጭት መልስ በየአካባቢው የሚደረዱ ህዝባዊ ውይይቶች ላይም አዘውትረን የምንሰማው ይህንኑ ነው፡፡ ደግሞም ሀቅ ነው፡፡ ታዲያ ምንድነው የሚያጋጨን? ሲባል መልሱ ግልጽ ነው፡፡ ያንን አብሮነታችንን አፍርሶ እርስ በእርስ አባልቶ ሊያጣፋን የሚሻ የጋራ ጠላታችን ወይም በግጭት ውስጥ ጥቅም የሚፈልግ ቁንጽል ፖለቲከኛ ወይም ብሄሩን መደበቂያ አድርጎ ከተጠያቂነት ለመሸሽ ላይ ታች የሚል ሌባ/ሙሰኛ ነው፡፡ ሲጠቃለል ግን የኛም ሆነ ከውጭ የመጣ ወገንን ደም በማቃባት ትርፍ የሚፈለግ ወይም የሚደሰት ያው ጠላታችን ነው፡፡

ራዕይ ራዕይ

ተልዕኮ ተልዕኮ

እሴቶች እሴቶች

© 2019 (ኢህአዴግ) የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር.