Back

የኦሮሞ ህዝብ የገዳ ስርዓት በዩኔስኮ በማይዳሰሱ የሰው ልጅ ወካይ ቅርስነት ተመዝግቧል

የኦሮሞ ህዝብ የአስተዳደር ስርዓት የሆነው የገዳ ስርዓት በዩኔስኮ በማይዳሰሱ የሰው ልጅ ወካይ ቅርስነት ተመዝግቧል፡፡ በከተማችን አዲስ አበባ ከህዳር 19 ቀን ጀምሮ ሲካሄድ በቆየው የዩኔስኮ ኮንፈረንስ በአገራችን የዴሞክራሲያዊ አስተዳደርን ማንም ሳይጀምር አስቀድሞ ይተገብር የነበረው የገዳ ስርዓትን በተመለከተ ኢትዮጵያ ከወከሉት ባሻገር የሌሎች አገር ተወካዮችም ጭምር ስለስርዓቱ ምንነት ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡   
በዩኔስኮ በማይዳሰሱ የሰው ልጅ ወካይ ቅርስነት የተመዘገበው የኦሮሞ ህዝብ የአስተዳደር ስርዓት የሆነው የገዳ ስርዓት ካሉት በርካታ እሴቶች መካከል ለእርቀ ሰላም ያለው ቦታ ከፍተኛ መሆኑ  ነው፡፡ በስርዓቱ በህብረሰተቡ ውስጥ በሚከሰቱ ግጭቶች የሰው ህይወት እንዳይጠፋና ሌሎች ችግሮችን እንዳያስከትል የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ በተጋጩት ወገኖች መካከል እርቀ ሰላም እንዲወርድ ይደረጋል፡፡
ከነዚህ መንገዶች መካከል የጉማ ስርዓት አንዱ ነው፡፡ ጉማ የሰውን ህይወት ያጠፋ ሰው ከሟች ወገኖች ጋር እርቀ ሰላም የሚያወርድበት መንገድ ነው፡፡ በእርቅ አውራጅ ሽማግሌዎች አማካይነት በሚደረገው በዚህ በጉማ ስርዓት የሚከፈለው የደም ካሳ የሟችን ህይወት ይተካል ተብሎ ታስቦ ሳይሆን በህዝቡ መካከል የነበረው የአብሮነት እሴት እንድጎለብትና ሀዝቡን ከእርስ በርስ እልቂት ለማዳን የሚደረግ የእርቀ ሰላም ሂደት ነው፡፡ ይህ ስርዓት የራሱ ህግና አተገባበር ያለው ሲሆን ከኦሮሞ ህዝብ በተጨማሪ በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎችም እርቀ ሰላምን ለማውረድ የሚያገለግል ስርዓት ነው፡፡
ሌላው በገዳ ስርዓት ውስጥ ጸብን ለማራቅና እርቀ ሰለምን ለማውረድ የሚደረገው ጥረት በክበር መሳሪያዎች አማካይነት የሚከናወን ሲሆን ‹‹ቦኩ›› ወይም ‹‹በትረ መንግስት››፣ከለቻና ጫጩ እንዲሁም በሲንቄ አማካይነት የሚፈጸሙ ናቸው፡፡
"ቦኩ" (በትረ መንግስት) በገዳ ስርዓት ውስጥ አባ ገዳዎች የሚይዙት በትር ሲሆን በህብረተሰቡ ውስጥ አለመረጋጋትና ግጭት ሲከሰት የሰው ህይወት እንደይጠፋ ህዝቡን ለማረጋጋት የሚያገለግል የክብር መሰሪያ ነው፡፡ በስርዓቱ መሰረት ግጭት በተከሰተበት ቦታ ላይ በመሄድ አባ ቡኩ/አባ ገዳ/ ‹‹ቡኩውን›› በመያዝ በሁለቱ ወገኖች መካከል እርቅ እንዲወርድ ያደርጋል፡፡ ይህ ካልተሳካ አባ ቦኩው በትሩን ከመሬት በማጋጨት ተራግሞ ሲለሚሄድ እርቀ ሰላሙን ላለመቀበል የሚደፍር አይኖርም፡፡
እንደ ቦኩ ሁሉ ከለቻ አባገዳዎች በግንባራቸው ላይ የሚያስሩት የክብር እቃ ሲሆን ጫጩ ደግሞ ከጉማሬ ቆዳ የተሰራና በዛጎል/ጨሌ/ ያጌጠ ባህላዊ የክብር እቃና የአባ ገዳው ባለቤት በእጇ የምትይዘው ነው፡፡ በጎሳዎች መካከል ግጭት ሲፈጠር ሁለቱን የክብር እቃዎች ይዘው በመሄድ በሁለቱ ወገኖች መካከል እርቀ ሰላም እንድወርድ ይደረጋል፡፡ የግጭቱ መንስኤ ውስብስብም ቢሆን ጉዳዩ በሌላ ጊዜ እንዲታይ ተደርጎ ሁለቱም ወገኖች በሰላም ይለያያሉ፡፡ ከለቻና ጫጩም ከእርቅ ሰላሙ በኋላ በክብር ወደ ቤት ይመለሳሉ፡፡
ሲንቄ (የሴቶች የክብር በትር) በገዳ ሰርዓት ውስጥ ትልቅ ስፋራ ከላቸው የክብር መሰሪያዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን ለሴት ልጅ በጋብቻዋ እለት ከእናቷ የሚለገስላት የክብር በትር ነው፡፡ ይህም በሴትነቷ የሚደርስባትን ተጽእኖ የምትካለከልበትና መብቷን የምትሳስከበርበት እንዲሁም ግጭት በተቀሰቀሰ ጊዜም እርቀ ሰላም ለማውረድ የሚያገለግል ነው፡፡ አንድ አባወራ በባለቤቱ ላይ ጥቃት ከፈጸመ ሴቶች ሲንቄያቸውን ይዘው በመውጣት ድርጊቱን በመቃወም ከተጎጂዋ ሴት ጎን ይቆማሉ፡፡ በዚህን ጊዜም አባገዳዎች ጥፋተኛውን አባ ወራ ቀጥተው፤ መክረው እንዲሁም ቃል አስገብተው ከቤተሰቦቹ ጋር በሰላም እንድኖር የሚደረግበት ስርዓት ነው፡፡
ከዚህም በሻገር በጎሳዎች መካከል ግጭት በተፈጠረ ጊዜ ሴቶች ሲንቄያቸውን ይዘው ሁለቱ ወገኖች እርቀ ሰላም እንዲያወርዱ የሚጠይቁበት ስርዓትም የገዳ ስርዓት አካል ነው፡፡ ሁለቱ ወገኖች የሴቶችን ተማጽኖ ሳይቀበሉ ከቀሩ ሴቶቹ ወደ ቤት አይመለሱም፡፡ በዚህም ልጆችና ከብቶች ሊጎዱ ስለሚችሉ እርቀ ሰላም ወርዶ ሴቶች ወደ ቤታቸው እዲመለሱ ለማድረግ አባገዳዎች ለሴቶቹ ተማጽኖ አጋርነታቸውን በመሳየት የተጋጩት ወገኖች እርቀ ሰላም እንዲያወርዱ ያደርጋሉ፡፡ ሲንቄ የሴቶች ክብር መገለጫ በመሆኑ ኃይማኖታዊና ባህላዊ ስነስርዓቶች በሚከናወኑበት ወቅት ሴቶች ይይዙታል፡፡


ኢህአዴግ

ኢህአዴግ አገር የመምራት ሃላፊነትን ከተረከበ ጊዜ ጀምሮ ከውስጥም ከውጭም የሚነሱ በርካታ ውጣ ውረዶችን ያስተናገደ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጣጣምና የህዝባችንን ሁለንተናዊ መለወጥ ታሳቢ ያደረገ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ስርዓት በማራመድ በውጭ ሃይል ተፅእኖ የሚጠመዘዝ ድርጅት አለመሆኑን ገና በጠዋቱ በተግባር ያሳየ ድርጅት ነው፡፡

ከደርግ ውድቀት ማግስት አገራችን የመበታተን ስጋት ውስጥ የነበረችበት ሁኔታ ቢኖርም መላ የሃገሪቱን ህዝቦች በማስተባበርና በብስለት በመምራት ዴሞክራሲያዊ አንድነቷ በፅኑ መሰረት ላይ እየተገነባ እንዲዘልቅ አስችሏል። ህገ መንግስታችን የአንድነታችንና የመከባበራችን ማሰሪያ ውል እንዲሆን በሚያስችል መልኩ በህዝብ ሙሉ ተሳትፎ ተቀርፆ በመፅደቁ ያንን የመበታተን ስጋት ተሻግረን በጋራ ለዘላቂ ለውጥ መረባረብ ጀምረናል።

ከኢህአዴግ ምክር ቤት ፅ/ቤት የተሰጠ መግለጫ

ኢህአዴግን ከግንባርነት ወደ አንድ ህብረ ብሄራዊ ውህድ ፓርቲ የማሸጋገር ጉዳይ በ1996 ዓ.ም ከተካሄደው 5ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ ጀምሮ በተከታታይ በተካሄዱት የድርጅቱ ጉባዔዎችና የተለያዩ ድርጅታዊ መድረኮች ሲነሳ የቆየ ጥያቄ እንደሆነ ይታወቃል። በሁሉም የኢህአዴግ መድረኮች በውህደቱ አስፈላጊነት ላይ ስምምነት እየተያዘበት የሄደ ሲሆን በየጉባዔዎቹ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ውህደቱን በጥናት ላይ ተመስርቶ ለመፈፀም የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎች ሲደረጉ ቆይተዋል። ይልቁንም በቅርብ ጊዜያት በተካሄዱ ጉባዔዎች ይነሳ የነበረው ቁልፍ ችግር በአፈፃፀሙ ላይ የታየው ከፍተኛ መጓተት ነበር።

ተጨማሪ ያንብቡ…

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህምድ የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊነት ዓለም አቀፉ ሕብረተሰብ ኢትዮጵያ ላይ ያለውንም ተስፋ ያመላከተ መሆኑን ተናገሩ፡፡

ፕሬዚዳንቷ ማምሻቸውን በጠቅላይ ሚኒስተሩ የኖቤል የሰላም ሽልማት የእንኳን ደስ አላችሁ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በዚህ መግለጫቸው ሀገር ውስጥ ላሉ እና በውጭ ሀገራት ለሚገኙ መላው ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንኳን ደስ አላችሁ መልክት አስተላፈዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ የ2019 የኖቤል የሠላም ሽልማትን በማሸነፍ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ሆነዋል ነው ያሉት፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ተወያዩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ዛሬ ጳጉሜን 1 ቀን 2011 ዓም ጠዋት በቢሯቸው ተወያይተዋል፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት በተደረገው ውይይት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከለውጡ ወዲህ መንግሥት ቤተ ክርስቲያንን በተመለከተ ያለውን አቋምና ያከናወናቸውን ተግባራት አውስተዋል፡፡ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስና ሌሎችም ሊቃነ ጳጳሳት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ ለሀገርና ለቤተ ክርስቲያን የተከናወኑ በጎ ተግባራትን በመዘርዘር ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ከኢህአዴግ ምክር ቤት ፅ/ቤት የተሰጠ መግለጫ

ኢህአዴግን ከግንባርነት ወደ አንድ ህብረ ብሄራዊ ውህድ ፓርቲ የማሸጋገር ጉዳይ በ1996 ዓ.ም ከተካሄደው 5ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ ጀምሮ በተከታታይ በተካሄዱት የድርጅቱ ጉባዔዎችና የተለያዩ ድርጅታዊ መድረኮች ሲነሳ የቆየ ጥያቄ እንደሆነ ይታወቃል። በሁሉም የኢህአዴግ መድረኮች በውህደቱ አስፈላጊነት ላይ ስምምነት እየተያዘበት የሄደ ሲሆን በየጉባዔዎቹ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ውህደቱን በጥናት ላይ ተመስርቶ ለመፈፀም የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎች ሲደረጉ ቆይተዋል። ይልቁንም በቅርብ ጊዜያት በተካሄዱ ጉባዔዎች ይነሳ የነበረው ቁልፍ ችግር በአፈፃፀሙ ላይ የታየው ከፍተኛ መጓተት ነበር።

ሀገራዊ አንድነታችንን በማጠናከር ለበለጠ ድል እንዘጋጅ

ኢትዮጵያ ከሶስት ሺኅ ዓመታት በላይ ዕድሜ ያላት ጥንታዊ ሀገር ናት፡፡ ሉአላዊነቷን ሳታስደፍር የቆየች የስልጣኔ መሰረት የሆነች ድንቅ ሀገርም ናት፡፡ እየተፈራረቁ የመጡት የውጭ ወራሪዎች የማሳፈር ታሪክዋ በዋናነት ዜጎቿ በብሄር፣ በሃይማኖት ሳይከፋፈሉ በሀገር ፍቅር ለመስዋዕትነት ዝግጁ መሆናቸው ነው፡፡

ወጣትነት በአዲስ ዓመት ዋዜማ!

በሀገራችን በተለያዩ መስኮች የወጣቶች አሻራ ደምቆ ይታይል፡፡ በተለያዩ የመሰረት ልማት ግንባታዎች፤ በጥናትና ምርምር እንዲሁም ሀገርን ከጠላት በመጠበቅ ረገድ ወጣቶች የማይተካ ሚና ተጫውተዋል፡፡ በመጫወትም ላይም ይገኛሉ፡፡ በሀገራችን በየዓመቱ በርካታ ወጣቶች በተለያዩ ሙያዎች ሰልጥነው ይመረቃሉ፡፡ከእነዚህ መካከል የቀሰሙትን ዕውቀት ወደ ተግባር በመቀየር ችግር ፈቺ ፈጠራዎችን በማበርከት በአካባቢው ባለው ቁሳቁስ በመጠቀም በቀላሉ ወደ ምርት መጠቀም ለማስቻል ጥረት የሚያደርጉ አሉ፡፡ በቁጥር ጥቂት ቢሆኑም ከራሳቸው አልፈው ለሌሎችን ዜጎች የሥራ የፈጠሩ አሉ፡፡

ውይይትና መደማመጥን በማጠናከር ሰላማችን እንጠብቅ!

የረጅም ዘመን የስልጣኔና ተምሳሌት የሆነችው ሀገራችን ዓለም በሁለት ገጽታዎች ያውቃታል፡፡ አንደኛው በምድራችን ውስጥ ከነበሩ ገናና እና አስደናቂ ስልጣኔዎች መካከል የአንዱ ባለቤት መሆንዋ ነው፡፡ የእነዚህን ስልጣኔዎች ማሳያ የሆኑ ሐውልቶች፣ ቅርሶች… ወዘተ የዚህ ህያው ማስረጃዎች ናቸው፡፡ አሁንም የዓላማችን የታሪክ ተመራማሪዎች ያሉፉት የስልጣኔ አሻራ ላይ የሚያደርጉት ጥናትና ምርምር እንደቀጠለ መሆኑን ስንመለከት ሐገራችን የነበረችበት የስልጣኔ ደረጃ መገንዘብ የሚያስችል ነው፡፡

የፌዴራል ስርዓቱ ሁሉንም ፍላጎቶች ማስተናገድ የሚችል ነው!

እነአሜሪካና ስዊዘርላንድ ፌዴራላዊ ስርዓትን ተቀብለው መተግበር ከጀመሩ ምዕተ አመት አስቆጥረዋል። እንደተባለው ስርዓቱ ሀገርን አደጋ ውስጥ የሚጥልና አንድነትን የሚያጠፋ ቢሆን ኖሮ ዛሬ አሜሪካም ሆነ ስዊዘርላንድ የሚባሉ አገራትን ላናይ እንችል ነበር። አሜሪካ እ.ኤ.አ. በ1789 በህገመንግስት የተረጋገጠ ፌደራላዊ ስርዓትን በሀገሯ ላይ እውን አድርጋለች። ስዊዘርላንድ ደግሞ እ.ኤ.አ በ1848 ስርዓቱን በህገመንግስቷ እውቅና ሰጥታ ዘርግታለች። ጀርመንም እ.ኤ.አ.በ1871 ፌዴራላዊ መንግስትን ይፋ አድርጋለች። በመቀጠልም ካናዳ፣ ቤልጂየም፣ ህንድ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ናይጄሪያ፣ ሱዳን፣ አርጀንቲና፣ ብራዚል፣ ሜክሲኮ፣ የቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ የተለያዩ ግዛቶች፣ ቼኮስሎቫኪያ፣ ከኮሚኒዝም መፈራረስ በኋላ የቀድሞዋ ሶቪየት ህብረት ወደ ፌዴራል ስርዓት በሂደት እንደተቀላቀሉ የዘርፉ ምሁራን ከጻፏቸው ሰነዶች መረዳት ይቻላል።

Visitorcounter Visitorcounter

Today       

113

       የዛሬ ጎብኚ

Yesterday       

183

       የትናንት ጎብኚ

This Month       

6509

       የዚህ ወር ጎብኚ

This Year       

230148

       የዚህ ዓመት ጎብኚ

Total        

403501

       አጠቃላይ ጎብኚ