ዜና ዜና

በሰብዓዊ መብት ጥሰት እና በሙስና የተጠረጠሩ 63 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው የፌደራል አቃቢ ህግ ገለጸ

27 በሙስና የተጠረጠሩ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሰራተኞች እና በሰብዓዊ መብት ጥሰት የተጠረጠሩ 36 የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሰራተኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸው የፌደራል አቃቤ ህግ ገለጸ፡፡ የፌደራል አቃቤ ህግ ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ እንተናገሩት ከሰብአዊ መብት አያያዝ ጋር ተያይዚ የተያዙ ተጠርጣሪዎች በ48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት መቅረብ ሲገባቸው በስውር እስር ቤቶች ውስጥ እንዲቆዩ ይደረግ እንደነበር ገልጸዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኤርትራው ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የሶማሊው ፕሬዘዳንት መሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ጎንደር ከተማ ገቡ፡፡

ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈ ወርቂና ፕሬዘዳንት ሙሃመድ አብዲላሂ አጼ ቴዎድሮስ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ የኤፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አሕመድን ጨምሮ የሶማሊ ክልል ፕሬዘዳንት ሙስጠፌ ዑመር እንዲሁም የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በቦታው በመገኘት አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ ጎንደር ከተማ ላይ የሚገኙት የኢትዮጵያ፣የኤርትራ እና የሶማሊያ መሪዎች ዛሬ ጎንደር ላይ የተለያዩ ቦታዎችን ጎብኝተዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ይበልጥ እየተጠናከረ የመጠው የሁለቱ አገራት ግንኙነት

ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶር አብይ አሕመድ ወደ ስልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ይፋዊ ንግግር ውስጥ ከኤርትራ መንግስት ጋር ያለውን ግንኙት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ወደሰላማዊ ሁኔታ ለመመለስ የሚፈልጉ መሆናቸውን ነው፡፡ በንግግራቸውም ለኤርትራ መንግስት ጥሪ በማድረግ ኢትዮጵያ የሁለቱን አገራት ግንኙነት ወደ አዲስ የሰላማዊ ምዕራፍ ማሸጋገር የሚቻላትን ያህል እንደምታደረግ አብስረው ነበር፡፡ ይህ ዜና በርካታ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራውያንን ያስደሰት ዜና ነበር፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ፕሬዝዳት ሳህለወርቅ ዘውዴ ቃለ መሃላ ፈፅመው ኃላፈነታቸውን በትጋትና በታማኝነት አገርና ህዝብን ለማገልገል ቃል ገብተዋል፡፡

አምባሳደር ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ላለፉት አመስት ዓመታት በኃላፊነት ላይ የነበሩትን ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመን በመተካት አገሪቱን በፕሬዝዳንትነት የሚመሩ ይሆናል፡፡ አምባሳደር ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ የድፕሎማሲ ታሪክ ከአገር እስከ አለም አቀፍ ተቋማት ድረስ ኢትዮጵያን በመወከል ያገለገሉ አለም አቀፍ ዲፕሎማት ናቸው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…