ዜና ዜና

የኢህአዴግ 11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ 7 የአቋም መግለጫዎችን በማውጣት ማምሻውን ተጠናቋል፡፡

ዲሞክራሲን በማስፋት ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር እርምጃዎች ተወስደዋል፡፡ ምህዳሩን ይበልጥ ለማስፋትና የመድብለ ፓርቲ ስርዓቱ እንዲጠናከር አበክረን እንሰራለን፡፡ • የፌዴራል ስርዓቱ ወሳኝ ሚና እየተጫወት ነው፡፡ ይሁን እንጂ አሁን አሁን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የዜጎች ሕገመንግስታዊ መብቶች ሲጣሱ ይታያል፡፡ ይህ እንዲቆምና የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ፤ የማንነት ጥያቄዎችም በህግ አግባብ እንዲፈቱ አቋም ላይ ደርሰናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ውይይቱ ከሻይ እረፍት በኋላም ቀጥሏል፡፡

ከጉባኤተኞች የሚቀርቡ ጥያቄዎች አሁንም እንደቀጠሉ ሲሆን የህግ የበላይነት፣ ሴቶችን በአመራርነት ማብቃት፣ የክልል ወሰን፣ አገራዊ አንድነት፣ ሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ የሜጋ ፕሮጀክቶች አፈፃፀም፣ የሰዎች በሰላም ተዘዋውሮ የመስራት ህገመንግስታዊ መብት፣ በአሰሪና ሰራተኛ መካከል ያሉ ኤጀንሲዎችን የተመለከቱና መሰል ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ 11ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ዛሬም እንደቀጠለ ነው፡፡

ትናንት በቀረበው የኢህአዴግ ምክር ቤት ሪፖርት ላይ በቡድን ውይይት ከተደረገበት በኋላ በዛሬው የከስዓት ውሎው ሪፖርቱን የተመለከተ ጥያቄዎችና አስተያየቶችን በመቅረብ ላይ ናቸው፡፡ በጉባኤው የተመረጠው ፕሬዚዲየም የውይይቱን አጀንዳዎችንም አፀድቋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ 11ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ መክፈቻ ባማረ ሁኔታ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

ሀገራዊ አንድነት ለሁለንተናዊ ብልፅግና በሚል መሪ ቃል ዛሬ በሀዋሳ ከተማ የመክፈቻ ስንስርዓት እየተካሄደ ነው፡፡ በድርጅታዊ ጉባኤ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የህዘብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ እና የደኢህዴን ሊቀመንበር ክብርት ሙፈርህያት ካሚል በታሪካዊ የትግል ምዕራፍ ውስጥ የሚካሄድ ጉባኤ በሀዋሳ ክልሉ እንዲያካሂደ መደረጉ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…