ዜና ዜና

የለውጥ ሂደቱን አጠናክሮ በማስቀጠል ለህዝቡ የሚመጥን አመራር መሰጠት እንደሚገባ ተመላከተ

ለውጡን ሁሉም በጋራ ወደተሻለ ምዕራፍ ማሻገር እንዳለበትና ህዝቡን የሚመጥን ቁመና ላይ በመሆን ለህዝብ ፍላጎቶች ተገቢውን ምላሽ መስጠት እንደሚገባ ጠቅሰዋል፡፡ የወሰን ጉዳይ በተመለከተ በሰጡት አስተያየት የአገራችን ህዝብ እርስ በእርስ የተጋመደ ህዝብ መሆኑን በመጠቅሰ ያለነው አንድ አገር ላይ ነውና ወርዶ ህዝቡን ማዳመጥ ያስፈልጋል፤

ተጨማሪ ያንብቡ…

ውይይቱ ነገም የሚቀጥል ይሆናል፡፡

በርካታ ሃሳቦች የተንሸራሸሩበት 11ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ የዛሬው ውሎው ተጠናቋል፡፡ ውይይቱ ነገም የሚቀጥል ይሆናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ 11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ 7 የአቋም መግለጫዎችን በማውጣት ማምሻውን ተጠናቋል፡፡

ዲሞክራሲን በማስፋት ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር እርምጃዎች ተወስደዋል፡፡ ምህዳሩን ይበልጥ ለማስፋትና የመድብለ ፓርቲ ስርዓቱ እንዲጠናከር አበክረን እንሰራለን፡፡ • የፌዴራል ስርዓቱ ወሳኝ ሚና እየተጫወት ነው፡፡ ይሁን እንጂ አሁን አሁን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የዜጎች ሕገመንግስታዊ መብቶች ሲጣሱ ይታያል፡፡ ይህ እንዲቆምና የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ፤ የማንነት ጥያቄዎችም በህግ አግባብ እንዲፈቱ አቋም ላይ ደርሰናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ውይይቱ ከሻይ እረፍት በኋላም ቀጥሏል፡፡

ከጉባኤተኞች የሚቀርቡ ጥያቄዎች አሁንም እንደቀጠሉ ሲሆን የህግ የበላይነት፣ ሴቶችን በአመራርነት ማብቃት፣ የክልል ወሰን፣ አገራዊ አንድነት፣ ሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ የሜጋ ፕሮጀክቶች አፈፃፀም፣ የሰዎች በሰላም ተዘዋውሮ የመስራት ህገመንግስታዊ መብት፣ በአሰሪና ሰራተኛ መካከል ያሉ ኤጀንሲዎችን የተመለከቱና መሰል ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…