ዜና ዜና

የኢህአዴግ 11ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ዛሬም እንደቀጠለ ነው፡፡

ትናንት በቀረበው የኢህአዴግ ምክር ቤት ሪፖርት ላይ በቡድን ውይይት ከተደረገበት በኋላ በዛሬው የከስዓት ውሎው ሪፖርቱን የተመለከተ ጥያቄዎችና አስተያየቶችን በመቅረብ ላይ ናቸው፡፡ በጉባኤው የተመረጠው ፕሬዚዲየም የውይይቱን አጀንዳዎችንም አፀድቋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ 11ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ መክፈቻ ባማረ ሁኔታ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

ሀገራዊ አንድነት ለሁለንተናዊ ብልፅግና በሚል መሪ ቃል ዛሬ በሀዋሳ ከተማ የመክፈቻ ስንስርዓት እየተካሄደ ነው፡፡ በድርጅታዊ ጉባኤ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የህዘብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ እና የደኢህዴን ሊቀመንበር ክብርት ሙፈርህያት ካሚል በታሪካዊ የትግል ምዕራፍ ውስጥ የሚካሄድ ጉባኤ በሀዋሳ ክልሉ እንዲያካሂደ መደረጉ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ራሱን አድሶ አዲስ ታሪክ የሚፅፍ ድርጅት!!

በሀዋሳ ከተማ ጉባኤውን ሲያካሄድ የቆየው የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲዊ ድርጅት/ደኢህዴን/ ‹‹የህዝቦች አንድነት፤ ለሁለንተናዊ ለውጥ፡፡›› በሚል መሪ ቃል ሲያካሄድ የነበረው 10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ የማዕከለዊና ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎችን በመምረት ትናንት ማምሻውን ተጠናቋል፡፡ የድርጅቱ ሊቀመንበር ወ/ሮ ሙፈርህያት ካሚል በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ እንደተናገሩት ጉባኤው ብዥታዎችን በማጥራት ወቅቱ የሚጠይቀውን የለውጥ አመራር እንደሚያደራጅ እምነቴ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ብአዴን ለአማራ ሕዝብና ለመድረኩ የሚመጥንና ለውጡን የሚያስቀጥል ቁመና ተላብሶ መውጣት እንደሚጠበቅበት ተገለፀ፡፡

የለውጡ ቀጣይት ለአማራ ሕዝቦች ተጠቃነትና ዴሞክራሲያዊ አንድነት; በሚል መሪ ቃል የብአዴን 12ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ በባህርዳር ከተማ እየተካሄደ ሲሆን በጉባኤው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እና የብአዴን ሊቀመንበር ባስተላለፉት መልእክት ብአዴን ለአማራ ሕዝብና ለመድረኩ የሚመጥንና ለውጡን የሚያስቀጥል ቁመና ተላብሶ መውጣት እንደሚጠበቅበት አመላክተዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…