ዜና ዜና

የብአዴን እህት ድርጅቶች የአጋርነታቸውን መልዕክት አስተላለፉ

በባሕዳር ከተማ እየተካሄደ ባለው የብአዴን 12ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ላይ በመገኘት የአጋነትና መልእክላቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በዚህ ጉባኤ ኦዲፒን በመወከል የተገኙት የኦዲፒ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ባስተላለፉት የአጋርነት መግለጫ ብአዴን የድርጅቱንና የአገሩቱን መጻኢ እድል የሚወስኑ ወሳኔዎችን እንደሚያስተላለፈ ጠቁመዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ጉባዔው የህዝቡን ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችሉ ውሳኔዎችን የሚተላለፉበት ይሆናል-ዶ/ር ደብረፅዮን

ዛሬ በተጀመረው 13ኛው የህወሓት ጉባዔ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የህወሓት ሊቀመንበር ጓድ ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በህወሓት መሪነት የተመዘገቡ ለውጦችን አንስተዋል፡፡ ጉባዔው የህዝቡን ጥያቄዎች ለመመለስ የሚያስችሉ ውሳኔዎች እንደሚወሰኑበትም አመልክተዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

እህት ፓርቲዎች በ13ኛው የህወሓት ድርጅታዊ ጉባዔው ላይ የድጋፍ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በ13ኛው የህወሓት ድርጅታዊ ጉባኤ ላይ የተገኙት የብአዴን፣ የኦዴፓ እና የደኢህዴን ተወካዮች ህወሓት በ13ኛው ጉባዔው ለሚያስተላልፋቸው ውሳኔዎች ተፈጻሚነት ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡ የእህት ፓርቲዎች ተወካዮች ባደረጉት ንግግር ህወሓት በኢትዮጵያ ተንሰራፍቶ የነበረውን ጭቆና ለማስወገድ ያካሄደውን ትግል በአድናቆት አውስተዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ኦዴፓ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ጉባኤውን አጠናቀቀ

ስያሜውን ወደ ኦዴፓ(የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት) የቀየረው ኦህዴድ በጅማ ከተማ 9ኛ የድርጅቱ ጉባኤ ‘‘የላቀ ሃሳብ ለተሻለ ድል'' በሚል መሪ ቃል ያካሄደ ሲሆን የኢሕአዴግ እና የኦህዴድ ሊቀ-መበር ጓድ ዶ/ር አብይ አህመድ ጨምሮ የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል፡፡ በጉባኤው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የድርጅቱ ሊቀመንበር ወደ ተሻለ አሸናፊነት ለመሸጋገር ከሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ጋር በጋራ በመሆን እና በማቀፍ ልንሰራ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…