ዜና ዜና

ኢህአዴግ በቡራዩና አከባቢዋ በተፈጠረው ግጭት በህይወትና በንብረት ላይ በደረሰው ጉዳት ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማው ይገልጻል

ከሰሞኑ በቡራዮና አከባቢዋ ባጋጠመው ሁከትና ግርግር በህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡ ይህ እየሆነ ያለው ድርጅታችን ኢህአዴግ ጥልቅ ተሃድሶ ካካሄደ በኃላ በድርጅታችን ሊቀመንበርና በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ መሪነት በርካታ ለውጦች እየተመዘገቡና ህዝቡም ከመንግስት ጎን ተሰልፎ ለውጡን ለማስቀጠል እየተረባረበ ባለበት ወቅት ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ 11ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ ከመስከረም 23 እስከ 25 ቀን 2011 ዓም ይካሄዳል

የኢህአዴግ 11ኛው መደበኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ከመስከረም 23 እስከ 25 ቀን 2011 ዓም በሀዋሳ ከተማ እንደሚካሄድ የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሄር ገለጹ፡፡ ጉባኤውን በማስመልከት ኃላፊዋ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ እንዳስታወቁት ጉበኤው "በልማታዊ ዴሞክራሲያዊ ማእቀፍ የለውጥ እንቅስቃሴን በማስቀጠል የአገራችንን ሕዳሴ እናረጋግጥ" በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ ሲሆን በተለያዩ አጀንዳዎችም የሚመክር ይሆናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ከኢህአዴግ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ

የኢህአዴግ ምክር ቤት ከመስከረም 4 እስከ 5 ቀን 2011 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታና ለውጡን በብቃት የመምራት አስፈላጊነት ዙሪያ እና በ11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ ረቂቅ ሪፖርት ላይ ተወያይቷል፡፡ የኢህአዴግ ም/ቤት በመጋቢት ወር ባካሄደው ስብሰባ ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች እና ያካሄደውን የአመራር ለውጥ ተከትሎ የተወሰዱ የለውጥ እርምጃዎች ህዝባዊ፣ ህገ-መንግስታዊ እና ኢህአዴጋዊ መሆናቸውን አረጋግጧል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ምክር ቤት ከመስከረም 4ቀን 2011 ዓም ጀምሮ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል

የኢህአዴግ ምክር ቤት ከመስከረም 04ቀን 2011 ዓም ጀምሮ መደበኛ ስብሰባውን የሚካሂድ ሲሆን ባለፈው ሳምንት በኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተገመገሙና ለምክር ቤቱ እንዲቀርቡ የተወሰኑ አጀንዳዎች ላይ እንደሚወያይ የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…