ዜና ዜና

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በቅርቡ በሚካሄደው 11ኛው ድርጅታዊ ጉባኤና ሀገራዊ ለውጡን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ በመምከር መደበኛ ስብሰባውን አጠናቀቀ

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከጳጉሜ 2 እስከ 4ቀን 2010 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ለ11ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ እየተደረገ ያለውን ዝግጅት እና በቀጣይ ሀገራዊ ለውጡን በብቃት ለመምራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክሯል፡፡ ስራ አስፈጻሚው በ10ኛው ድርጅት ጉባኤ በድርጅትና በመንግሰት ስራዎች ያስቀመጣቸው አቅጣጫዎች አፈጻጸምን ሪፖርት በመገምገም የ11ኛው ጉባኤ አቅጣጫዎች ላይም የመከረ ሲሆን የ11ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ "ሃገራዊ አንድነት፥ ለሁለንተናዊ ብልፅግና'' በሚል መሪ ቃል የሚያካሂደዉ ግምገማ፣ የሚያስቀምጣቸዉ አቅጣጫዎችና ዉሳኔዎች የሚኖራቸዉ ፋይዳ እጅግ ከፍተኛ መሆኑን አስቀምጧል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ከኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ከነሀሴ 14 እስከ 16/2010 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የጥልቅ ተሃድሶውን አፈፃፀምና ያስገኘውን ውጤት በተለመደው ድርጅታዊ ባህል፣ ዴሞክራሲያዊነትን በተላበሰ እና በሰከነ አግባብ በጥልቀት ገምግሟል፡፡ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የጥልቅ ተሃድሶውን ተከትሎ የተወሰዱ የለውጥ...

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል በሆኑት በጓድ ተስፋዬ ጌታቸው ህልፈተ ህይወት የኢሕአዴግ ምክር ቤት ፅ/ቤት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ይገልፃል፡፡

ጓድ ተስፋዬ ጌታቸው ለራሳቸው እንኳን ጊዜ ሳይሰጡ ያደረባቸውን ህመም በመታገል እስከ እለተ ሞታቸው ድረስ በብአዴን/ኢሕአዴግ አመራርነታቸው የተሰጣቸውን ህዝባዊና ድርጅታዊ ሃላፊነት በቅንነትና በብቃት የተወጡ የድርጅታችን በሳልና ቆራጥ አመራር ናቸው፡፡ የአማራ ክልል ህዝብ አሁን ለደረስንበት የለውጥ፣...

ተጨማሪ ያንብቡ…

ከኢህአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት የተሰጠ የሀዘን መግለጫ

በ ዛሬው ዕለት ሐምሌ 19 ቀን 2010 ዓም የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ታውቋል፡፡ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ዕውን እንዲሆን ከኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት የተሰጣቸውን...

ተጨማሪ ያንብቡ…