ዜና ዜና

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዶ/ር አብይ አህመድን የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰየመ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 3ኛ ዘመን 2ኛ ልዮ ስብሰባ ዶ/ር አብይ አህመድን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር አድርጎ ሰየመ፡፡ ዶ/ር አቢይ አህመድ በምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከተሰየሙ በኋላም ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡ ተመራጩ ጠቅላይ ሚንስትር ውጤት ያመጡ አሰራሮች ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆኑንና ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ ማማሻያ በማድረግ የተሻለች ኢትዮጵያን ለመፍጠር ይሰራል ብለዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ከኢህአዴግ ምክር ቤት የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫ

የኢህአዴግ ምክር ቤት ከመጋቢት 11 ቀን እስከ መጋቢት18 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል፡፡ በዚህ ስብሰባ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ባቀረባቸው ሁለት ሪፖርቶችና ከድርጅታችን ሊቀ መንበር የስራ መልቀቂያ ጋር በተያያዘ የመተካካት አጀንዳ ላይ ሰፊ ውይይት አካሂዶ ስብሰባውን በመግባባትና በአንድነት መንፈስ አጠናቋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ምርጫው ኢሕአዴግ ያሸነፈበት፣ የመስመራችን ሃያልነት የተረጋገጠበት ነው - ጓድ ሽፈራው ሽጉጤ

የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴና የኢሕአዴግ ምክር ቤት በውስጠ ዴሞክራሲ መዳከም የተነሳ በድርጅቱ ውስጥ የተፈጠሩ ፀረ ዴሞክራሲያዊ አካሄዶችን በጥልቀት በመገምገም ችግሮቹ እንዲታረሙና ዳግም እንዳይከሰቱ የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን ማስቀመጣቸውን የኢሕአዴግ ፅ/ቤት ሃላፊ ጓድ ሽፈራው ሽጉጤ አስታወቁ።

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ እንደቀጠለ ነው

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ) ምክር ቤት ስብሰባ ከባለፈው ማክሰኞ መጋቢት 11 ቀን 2010 ዓም ጀምሮ በመካሄድ ላይ ነው፡፡ ምክር ቤቱ በስብሰባው በኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ተገምግሞ በቀረበለት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሪፖርት፣ የእያንዳንዱ ብሄራዊ ድርጅት የጥልቅ ተሃድሶ ሂደት አፈጻጸም እና ለዕይታ በሚጠቅም ሰነድ ላይ በዝርዝር ይወያያል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…