ዜና ዜና

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ 27ኛውን የግንቦት 20 የድል በዓል ምክንያት በማድረግ ለመላው የሀገራችን ህዝቦች ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ህዝቦች፤ እንኳን ለ27ኛው አመት የግንቦት 20 ድል በአል በሰላም አደረሳችሁ! 27ኛውን የግንቦት 20 የድል በዓል ስናከብር ከውስጣችንም ሆነ ከውጪያችን አስታርቀውን ለራሳችንም ሆነ ለሌላው አዎንታዊ እይታን በሚያስታጥቁን መልካም ተግባራት ታጅበን እንዲሆን ከዚህ በፊት ከነበረው በተጨማሪ የሚከተሉትን 6 ጉዳዮች በመከወን እንዲሆን ከተለየ ፍቅርና አክብሮት ጋር ጥሪዬን አቀርባለሁ፡:

ተጨማሪ ያንብቡ…

በሀገሪቱ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የተለያዩ የለውጥ እርምጃዎች ይወሰደሉ

በሀገራችን ባለፉት ሁለትና ከዛ በላይ ዓመታት የሰላም መደፈርስ ሁኔታ ታይቷል፡፡ ኢህአዴግ ያጋጠመውን የሰላም መደፍረስ ችግር ለመፍታት የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ እና ምክር ቤት ደረጃም የጥልቅ ተሃድሶ ሂደቱን አጠናክሮ በማስቀጠልና በድርጅትና በመንግስት ውስጥ የሚታዩ...

ተጨማሪ ያንብቡ…

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዶ/ር አብይ አህመድን የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰየመ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 3ኛ ዘመን 2ኛ ልዮ ስብሰባ ዶ/ር አብይ አህመድን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር አድርጎ ሰየመ፡፡ ዶ/ር አቢይ አህመድ በምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከተሰየሙ በኋላም ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡ ተመራጩ ጠቅላይ ሚንስትር ውጤት ያመጡ አሰራሮች ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆኑንና ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ ማማሻያ በማድረግ የተሻለች ኢትዮጵያን ለመፍጠር ይሰራል ብለዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ከኢህአዴግ ምክር ቤት የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫ

የኢህአዴግ ምክር ቤት ከመጋቢት 11 ቀን እስከ መጋቢት18 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል፡፡ በዚህ ስብሰባ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ባቀረባቸው ሁለት ሪፖርቶችና ከድርጅታችን ሊቀ መንበር የስራ መልቀቂያ ጋር በተያያዘ የመተካካት አጀንዳ ላይ ሰፊ ውይይት አካሂዶ ስብሰባውን በመግባባትና በአንድነት መንፈስ አጠናቋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…