ዜና ዜና

ምርጫው ኢሕአዴግ ያሸነፈበት፣ የመስመራችን ሃያልነት የተረጋገጠበት ነው - ጓድ ሽፈራው ሽጉጤ

የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴና የኢሕአዴግ ምክር ቤት በውስጠ ዴሞክራሲ መዳከም የተነሳ በድርጅቱ ውስጥ የተፈጠሩ ፀረ ዴሞክራሲያዊ አካሄዶችን በጥልቀት በመገምገም ችግሮቹ እንዲታረሙና ዳግም እንዳይከሰቱ የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን ማስቀመጣቸውን የኢሕአዴግ ፅ/ቤት ሃላፊ ጓድ ሽፈራው ሽጉጤ አስታወቁ።

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ እንደቀጠለ ነው

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ) ምክር ቤት ስብሰባ ከባለፈው ማክሰኞ መጋቢት 11 ቀን 2010 ዓም ጀምሮ በመካሄድ ላይ ነው፡፡ ምክር ቤቱ በስብሰባው በኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ተገምግሞ በቀረበለት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሪፖርት፣ የእያንዳንዱ ብሄራዊ ድርጅት የጥልቅ ተሃድሶ ሂደት አፈጻጸም እና ለዕይታ በሚጠቅም ሰነድ ላይ በዝርዝር ይወያያል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ የአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ መስመር በሚያጠናከር መልኩ በአመራሩ መካከል የአመለካከት አንድነት በተሸለ ሁኔታ ፈጥሮ ተጠናቅቋል

ከመጋቢት 2 እስከ 10 ቀን 2010 ዓም ሲካሄድ የቆየው የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ በብሄራዊ ድርጅቶች መካከል የአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ መስመር የአመለካከት አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ በጥልቀት ተፈትሾ በመግባባት መጠናቀቁን የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት በላከልን መግለጫ አመለከተ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ በመጪው እሁድ ይጀመራል

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ከመጋቢት 2 ቀን 2010 ዓ/ም ጀምሮ እንደሚካሄድ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት ኃላፊ ጓድ ሽፈራው ሽጉጤ ገለጹ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…