ዜና ዜና

በኢሕአዴግና እና በሱዳኑ ናሽናል ኮንግረንስ ፓርቲ (NCP) መካከል ያለው የፓርቲ ለፓርቲ ግንኙነት እየተጠናከረ መምጣቱን በኢሕአዴግ ምክር ቤት ፅ/ቤት የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪክ ማህበራት አስተባባሪ ጓድ አምባሳደር ደግፌ ቡላ ተናገሩ።

ጓድ አምባሳደር ደግፌ በካርቱም በተካሄደው የሱዳን ናሽናል ኮንግረንስ ፓርቲ ኮንፈረንስ መክፈቻ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር የረጅም ዘመናት ታሪክ ያለው የኢትዮጵያና ሱዳን ግንኙነት በመንግስታቱና በህዝቦቹ መካከል ባለው ግንኙነት ብቻ ሳይወሰን በመሪ ፓርቲዎቹ ደረጃም ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል። የኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ ኢሕአዴግ ግንኙነቱ ከዚህም በላቀ መልኩ እንዲጎለብት ፍላጎታቸው መሆኑንም አስታውቀዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባለፈው አመት በድርጅታችን የተጀመረውን በጥልቀት የመታደስ ንቅናቄ አፈፃፀም በዝርዝር መገምገም ጀምሯል፡፡

በድርጅታችን ኢሕአዴግ የቆየ ባሕል መሰረት አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ፕሮግራሙን ተግባራዊ ለማድረግ በሚያካሂደው የትግል ሂደት የሚያጋጥሙትን ጉድለቶች ሰፊ ጊዜ ሰጥቶ በጥልቀት ይገመግማል። ግምገማውን መሰረት በማድረግም ራሱን በራሱ ያርማል። እነሆም የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ቀደም ሲል የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት የነበሩና የተተኩ ነባር ታጋዮችን ባከተተ አግባብ ከታህሳስ 3 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ግምገማ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

ኢህአዴግ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት የሚያስችሉ ተግባራት እያከናወነ መሆኑን ገለጸ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ) ባለፈው በዓመት በተጀመረው የጥልቅ ተሃድሶ ሂደት በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የፖለቲካ ምህዳር ለማስፋትና የኃሳብ ብዙሃነትን የሚስተናገድበትን አግባብ ይበልጥ ለማስፋት የሚያስችሉ ተግባራት በማከናወን ላይ እንደሚገኝ የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ኃላፊና የድርጅቱ የስራ አስፈጻሚ አባል ጓድ ሽፈራው ሽጉጤ ገለጹ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ብአዴን ከዴሞክራሲያዊ ድርጅቶች ጋር ያለውን አንድነት በማጠናከር ለበለጠ ድል እንደሚተጋ አስታወቀ

የብሄረ አማራ ዴሞክረሲያዊ ንቅናቄ(ብአዴን) ከሌሎች ዴሞክራሲ ድርጅቶችና የለውጥ ኃይሎች ጋር ያለውን አንድነት በማጠናከር በሁሉም መስኮች የተጀመሩ ለውጦችን ከዳር ለማድረስ ጠንክሮ እንደሚሰራ የድርጅቱ ሊቀ መንበርና የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጓድ ደመቀ መኮነን አስታወቀ፡፡ ኢህዴን/ብአዴን የተመሰረተበት 37ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ነባር ታጋዮች፣ የድርጅቱ አባላትና ደጋፊዎች በተገኙበት

ተጨማሪ ያንብቡ…