ዜና ዜና

10ኛው የሰንደቅ ዓላማ በዓል በድምቀት ተከበረ

10ኛው የሰንደቅ አላማ ቀን “ራዕይ ሰንቀናል፤ለላቀ ድል ተነስተናል” በሚል መሪ ቃል በድምቀት ተከብሯል፡፡ በአዲስ አበባ ስታዲዬም በተከበረው በዓል ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ሰንደቅ አላማ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ዘመን ተሻጋሪ ትግል ያስገኘው ውጤት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ሰንደቅ አላማ በመፈቃቀድ ላይ ለተመሰረተው ዴሞክራሲያዊ አንድነት የቃል ኪዳን አርማ መሆኑን ጠቅሰዋል። ላለፉት 10 ዓመታት ተግባራዊ በተደረጉ የተለጠጡ የልማት ዕቅዶች ለመተግበር ርብርብ ሲደረግ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡ በዚህም ኢትዮጵያ በአለማቀፍ መድረኮች ላይም ያ ላትሚና እያደገ መምጣቱን ፕሬዝዳንቱ አመልክተዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ ሥራ አስፈጻሚ የጥልቅ ተሃድሶ አተገባበርን ገመገመ

በመድረኩ ላይ የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ ሊቀመንበር ጓዲት ሙፈርህያት ካሚል እንደገለጹት የኪራይ ሰብሳቢነት መገለጫ የሆኑትን የጠባብነት፣ትምክህት፣ሙስና፣የሃይማኖት አክራርነት የመሳሳሉትን ችግሮች ለሴቶች ተጠቃሚነት ተግዳሮች መሆናቸው በማመን ትግል ለማድረግ የሚያስችል እንቅስቃሴ መደረጉንም ተናግረዋል፡፡ እነዚህ ችግሮች በጥቂት አመታት የተፈጠሩ ሳይሆኑ ለዘመናት ሲንከባለሉ የመጡ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ህግ ላይ ውይይት ማድረጋቸውን ቀጥለዋል

ሀገር አቀፍ የፖቲካ ፓርቲዎች ባለፈው ሳምምንት የጀመሩት የምርጫ ስርአቱ ምን አይነት መልክ ሊኖረው ይገባል በሚል አጀንዳ እያደረጉት ያለውን ውይይት ዛሬም ቀጥሎ ተካሂደዋል፡፡ ከድርድሩ በኃላ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ የሰጡት የፖለቲካ ፓርቲዎች ደርድር የሚድያ ኮሚቴ አባላት እንደገለጹት የድርድር ሂደቱ ጥሩ በሚባል መንፈስ በመደማመጥ እየተካሄደ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ኢትዮጵያ ድርቅን በመቋቋም ረገድ ውጤታማ ተግባራትን ማከናወኗን አይ ኤም ኤፍ አስታወቀ

ኢትዮጵያ ድርቅን ለመቋቋም ያደረገችው እንቅስቃሴ ውጤታማ እንደሆነ ዓለም አቀፋ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ትናንት ባወጠው መረጃ አመልክቷል፡፡ አይ ኤም ኤፍ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ አፈፃፀም እና ቀጣይ ሁኔታዎች የገመገመበትን ጥናት የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ይፋ ባደረገበት ሪፖርቱ መንግስት በአገሪቱ ተከስቶ ለነበረው ድርቅ ከተለያዩ አካላት ጋር በመሆኑ ምላሽ ለመስጠት ያከናወናቸው ተግባራት በአደጋው በሰው ህይወት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ማድረጉንና ውጤታማ መሆኑን አስታውቋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…