ዜና ዜና

በጓድ አቶ መለሰ አለሙ የኢህአዴግ ጽ/ቤት ም/ሀላፊ ሚኒስትር የተመራ የልኡካን ቡድን በቻይና የስራ ጉብኝት እያደረገ ነው።

በድርጅታችን ኢህአዴግ በተለያየ የድርጅት ስራ ተመድበው እያገለገሉ የሚገኙና 13 አባላትን ያካተተው ይህ የሉእካን ቡድን በቻይና ቤጅንግ ከተለያዩ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ አመራሮች ጋር ለአስር ቀናት የሚቆይ የልምድ ልውውጥ እያደረገ ይገኛል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢሕአደግ ሴቶች ሊግ 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በመቀሌ ከተማ ያካሄዳል፡፡

የኢሕአዴግ ሴቶች ሊግ 4ኛ መደበኛ ጉባኤን ከታህሳስ 7 እስከ ታህሳስ 9 ቀን 2011 ዓ.ም በመቀሌ ከተማ #በተደራጀ የሴቶች ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለሁለንተናዊ አገራዊ ለውጥ; በሚል መሪ ቃል እንደሚካሄድ የኢሕአዴግ ሴቶች ሊግ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሠዓዳ ኡስማን ገለጹ፡፡ እንደ ኃላፊዋ ገለጻ ጉባኤ በአጠቃለይ ከ700 አባላት የሚሳተፉበት ሲሆን 620 በድምጽ የሚሳተፉ 20ዎቹ ደግሞ ያለድምጽ የሚሳተፉት ተጋባዥ እንግዶች ናቸው ብለዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የሱዳን ፕሬዘዳንት ኦማር ሃሰን አልበሽር እና የጁቡቲ ፕሬዘዳት እስማኤል ዑመር ጊሌ ጅማ ከተማ ገቡ፡፡

የጂቡቲ ፕሬዘዳንት እስማኤል ዑመር ጊሌ ፣ የሱዳን ፕሬዘዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር በዛሬ እለት ጅማ ሲደርሱ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ጨምሮ ሌሎች የስራ ኃላፊዎች ጅማ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አሕመድ ጨምሮ ፕሬዘዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር እና ፕሬዘዳት እስማኤል ጊሌ በጅማ ከተማ የተለያዩ የልማት ሥራዎች እየጎበኙ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

13ኛ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች በዓል በአዲስ አበባ በዛሬው ዕለት በድምቀት ተከበረ፡፡

የኢፌዲሪ ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታደሰ ጫፎ፤ የፌደሬሽን ም/ቤት አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማን ጨምሮ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በበዓሉ ተገኝተዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…