ዜና ዜና

አብሮነት፣ መቻቻልና ሰላም ታላቅ ሀገር ለመገንባት ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተናጋጅነት በተከበረው 13ኛው የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ታላቅ ሀገር ለመገንባት ከሰላምና ከአብሮነት ውጪ አማራጭ እንደሌለ ተገለፀ። በበዓሉ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ መቻቻል አብሮ ለመኖር መሰረታዊ ነገር ነው ብለዋል። አያይዘውም ልዩነትን ከሚያሰፉ አስተሳሰቦች በመውጣት በጋራ ጉዳዮች ላይ የሀገሪቱ ህዝብ አብሮ በመቆም መስራት እንዳለበት ተናግረዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

የብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን የኢትዮጵያዊነትን ልዩ ልዩ ፀጋዎች እያሳየን፣ እያከበርንና እየጠበቅን የምናከብረው በዓል ነው - ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ

ኤፍ ቢሲ እንደዘገበው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ 13ኛውን የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን ምክንያት በማድረግ ለሀገሪቱ ህዝቦች መልዕክትን አስተላልፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው ኢትዮጵያ መንትያና ምትክ የሌላት አንዲት ሀገር ብትሆንም፥ ኢትዮጵያውያነት ግን በብዙ ህብር የሚገለፅ የዚህች ሀገር ዜጎች ድምር ፀጋ መሆኑን ጠቁመዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

13ኛው የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀንን በአዲስ አበባ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ ነው

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነትና በአዲስ አባበ ከተማ አስተዳደር አስተናጋጅነት ‘በብዝኃነት የደመቀ ኢትዮጵያዊ አንድነት’’ በሚል መሪ ቃል ዘንድሮ ለ13ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረስቦች እና ህዝቦች ቀን ምክነያት በማድረግ የአገራችን ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ወደ አዲስ አበባ እየተመሙ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች ጽህፈት ቤቱ ተልዕከውን በተጠናከረ መልኩ መወጣት በሚችልበት ሁኔታ ላይ በዛሬው ዕለት ውይይት አካሂደዋል፡፡

የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት በሀገራችን የተጀመረውን ሁሉን አቀፍ ለውጥና በ11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ በተቀመጠው የሪፎርም አቅጣጫ መሰረት ወደ ለውጥ እንቅስቃሴ መግባቱንም በውይይቱ ወቅት ተገልጻል፡፡ ጽ/ቤቱ በሀገራችን በመተግበር ላይ ያለውን ለውጥ ለመደገፍ የሚያስችል አሰራራና አደረጃጀት ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ነው በውይይቱ ተነስቷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…