ዜና ዜና

ይበልጥ እየተጠናከረ የመጠው የሁለቱ አገራት ግንኙነት

ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶር አብይ አሕመድ ወደ ስልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ይፋዊ ንግግር ውስጥ ከኤርትራ መንግስት ጋር ያለውን ግንኙት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ወደሰላማዊ ሁኔታ ለመመለስ የሚፈልጉ መሆናቸውን ነው፡፡ በንግግራቸውም ለኤርትራ መንግስት ጥሪ በማድረግ ኢትዮጵያ የሁለቱን አገራት ግንኙነት ወደ አዲስ የሰላማዊ ምዕራፍ ማሸጋገር የሚቻላትን ያህል እንደምታደረግ አብስረው ነበር፡፡ ይህ ዜና በርካታ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራውያንን ያስደሰት ዜና ነበር፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ፕሬዝዳት ሳህለወርቅ ዘውዴ ቃለ መሃላ ፈፅመው ኃላፈነታቸውን በትጋትና በታማኝነት አገርና ህዝብን ለማገልገል ቃል ገብተዋል፡፡

አምባሳደር ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ላለፉት አመስት ዓመታት በኃላፊነት ላይ የነበሩትን ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመን በመተካት አገሪቱን በፕሬዝዳንትነት የሚመሩ ይሆናል፡፡ አምባሳደር ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ የድፕሎማሲ ታሪክ ከአገር እስከ አለም አቀፍ ተቋማት ድረስ ኢትዮጵያን በመወከል ያገለገሉ አለም አቀፍ ዲፕሎማት ናቸው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

አምባሳደር ሳህለ ወርቅ ዘወዴ የኢፌዲሪ ፕሬዘዳንት ሆነው ተመረጡ

የሕዝብ ተወካዮችና የፌደሬሽን ም/ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው ስብሰባ አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴን የኢፌዲሪ ፕሬዘዳንት አድርጎ መርጧል፡፡ ተመራጭዋ ፕሬዚዳት አምሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ በሁለቱ ምክር ቤት ፊት ንግግር አድርገዋል፡፡ ፕሬዘዳት ሆነው በመመረጣቸው የተሰማቸውን ደስታ የገለጹ ሲሆን ለተሰናባቹ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ በሥልጣን ዘመናቸውን ለአገራቸው ላበረከቱት አስተዋጽዎ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ክቡር የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ላይ ያደረጉት ንግግር

አሮጌውን ዓመት ሸኝተን ወደ አዲሱ ዓመት በተሸጋገርንበት በዚህ በመስከረም ወር የመጨረሻ ሰኞ የኢፌዴሪ ሕገ-መንግስት በሚደነግገው መሠረት የሁለቱ ምክር ቤቶች የሥራ ዘመን መጀመርን በይፋ ለማብሰር በሚከናወነው የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝቼ ንግግር እንዳደርግ በመቻሌ ልባዊ ደስታ የተሰማኝ መሆኑን ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…