ዜና ዜና

13ኛው የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀንን በአዲስ አበባ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ ነው

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነትና በአዲስ አባበ ከተማ አስተዳደር አስተናጋጅነት ‘በብዝኃነት የደመቀ ኢትዮጵያዊ አንድነት’’ በሚል መሪ ቃል ዘንድሮ ለ13ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረስቦች እና ህዝቦች ቀን ምክነያት በማድረግ የአገራችን ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ወደ አዲስ አበባ እየተመሙ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች ጽህፈት ቤቱ ተልዕከውን በተጠናከረ መልኩ መወጣት በሚችልበት ሁኔታ ላይ በዛሬው ዕለት ውይይት አካሂደዋል፡፡

የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት በሀገራችን የተጀመረውን ሁሉን አቀፍ ለውጥና በ11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ በተቀመጠው የሪፎርም አቅጣጫ መሰረት ወደ ለውጥ እንቅስቃሴ መግባቱንም በውይይቱ ወቅት ተገልጻል፡፡ ጽ/ቤቱ በሀገራችን በመተግበር ላይ ያለውን ለውጥ ለመደገፍ የሚያስችል አሰራራና አደረጃጀት ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ነው በውይይቱ ተነስቷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

“የምንናገረው ዴሞክራሲ የምንኖርበት መሆን አለበት” ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ

በሀገራችን ዴሞክራሲ ባህል በማሳደግና የዴሞክራሲ ግንባታን በማጠናከር ዘላቂ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት እንደሚገባ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገለጹ፡፡ በፖለቲካ ድርጅቶች መካከል በሀገራዊ ጉዳዮች ዙርያ የሚደረጉ ውይይቶች አካሄድ የተመለከተ ውይይት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ተካሂዷል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚካሄደውን ውይይትና አጠቃላይ የሀገራችን የዴሞክራሲ ሁኔታ የሚመለከት ገለጻ አድርገዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይን በተመለከተ ከኢሕአዴግ ምክር ቤት ፅ/ቤት የተሰጠ መግለጫ

ድርጅታችን ኢሕአዴግ መላውን የኢትዮጵያ ሕዝቦች ትግል በማስተባበር ዘርፈ ብዙ ለውጦችን ማስመዝገብ የቻለ ድርጅት ነው። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የሀገራችንን ሕዝቦችና የተለያዩ የህዝብ አደረጃጀቶችን ለቅሬታና ለምሬት የዳረጉ ጥፋቶች በአመራር ዘመኑ እንደተፈጸሙ አበክሮ ይገነዘባል። ለተከታታይ አመታት የጥልቅ ተሃድሶ መድረኮችን በማካሄድ የችግሮቹን ምንጭና መፍትሄዎች ለመለየት ሲሰራ የቆየውም ከዚሁ በመነሳት ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ…