ዜና ዜና

የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በዛሬው እለት በደማቅ የመክፈቻ ስነስርአት በመቐለ ከተማ ተጀምሯል ።

የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በዛሬው እለት በደማቅ የመክፈቻ ስነስርአት በመቐለ ከተማ ተጀምሯል ።

"የተደራጀ የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለሁለንተናዊ አገራዊ ለውጥ" በሚል መሪ ቃል የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በመቐለ ከተማ እየተካሄደ ሲሆን የሊጉ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የትግራይ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

የተደራጀ የሴቶች ተሳትፎ መኖር ለሀገራዊ ለውጡ የጎላ ፋይዳ እንዳለው የተገፀ ሲሆን ድርጅታችን ኢህአዴግ በሴቶች ዙሪያ እያደረገው ላለው እንቅስቃሴ ጉባኤው ተጨማሪ ጉልበት እንደሚሆን ተጠቅሷል።

ለ 3 ተከታታይ ቀናት በሚቆየው በዚህ ጉባኤ ላይ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተወጣጡ በተለያየ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሴቶች ተሳታፊ ሆነዋል።

መድረኩ እንደ ድርጅት ለሴቶች የተሰጠውን ትኩረት አጠናክሮ የሚያስቀጥል አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።

የጉባኤውን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ ሊቀመንበሯ ጓዲት ሙፈሪያት ካሚል ላለፉት 2 አመት ተኩል በተለያዩ አቅጣጫዎች ከባድ ትግል መደረጉን እና በአሁን ሰአት ሀገራችን ኢትዮጵያ በአስጊ እና በአጓጊ ሁኔታዎች መከበቧን ጠቅሰው እንደ ሀገር የሚታዩ ተግዳሮቶችን መቅረፍ እንዲቻል ሴቶች የበኩላቸውን አስተዋፆ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

"እኛ ሴቶች ተፈጥሯዊ ባህሪያችን ለሰላም የቀረበ ነው" ያሉት ጓዲት ሙፈሪያት ካሚል ህዝብ እንደ ህዝብ ጥላቻ እንደሌለበት እና መቼም ቢሆን ሴቶች ለሀገራዊ ሰላማችን ቅድሚያ ሰጥተን በመንቀሳቀስ ሀገራችን ከፊቷ የተደቀነባትን ተግዳሮቶችን እናፅዳ በማለት ለጉባኤው ተሳታፊዎች ገልፀዋል።