እንወያይ እንወያይ

የኢሕአደግ ሴቶች ሊግ 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በመቀሌ ከተማ ያካሄዳል፡፡

የኢሕአዴግ ሴቶች ሊግ 4ኛ መደበኛ ጉባኤን ከታህሳስ 7 እስከ ታህሳስ 9 ቀን 2011 .ም በመቀሌ ከተማ #በተደራጀ የሴቶች ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለሁለንተናዊ አገራዊ ለውጥ; በሚል መሪ ቃል እንደሚካሄድ የኢሕአዴግ ሴቶች ሊግ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሠዓዳ ኡስማን ገለጹ፡፡

እንደ ኃላፊዋ ገለጻ ጉባኤ በአጠቃለይ ከ700 አባላት የሚሳተፉበት ሲሆን 620 በድምጽ የሚሳተፉ 20ዎቹ ደግሞ ያለድምጽ የሚሳተፉት ተጋባዥ እንግዶች ናቸው ብለዋል፡፡

የጽ/ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ ሰዓዳ እንደገለጹት ሴት ሚኒስተሮችን ጨምሮ ከተለያዩ የሕዝብረተሰብ ክፍሎች የተወጣጡ ሴት ተጋበዥ እንግዶች እንደሚገኙም ገልጸዋል፡፡