ትኩስ ዜና

የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ የአቋም መግለጫ የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ በመቐለ ከተማ እያካሄደ ባለው የሊጉ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ጓዲት መሰረት መስቀሌን ከደኢህዴን በሊቀመንበርነት፣እንዲሁም ጓዲት መስከረም አበበን ከአዴፓ ምክትል ሊቀ መንበር አድርጎ መርጧል። የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ የአገሪቱን ሰላም በማስጠበቅ ሂደት ውስጥ ግንባር ቀደም ሆኖ ለመንቀሳቀስ መወሰኑ ተገለፀ የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬም እንደቀጠለ ነው፡፡ የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በዛሬው እለት በደማቅ የመክፈቻ ስነስርአት በመቐለ ከተማ ተጀምሯል ። የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) ሴቶች ሊግ ጀግኒት! ከማጀት እስከ አደባባይ እድሉን እንጠቀምበት ትንሽ በሚመስል የግለሰብ አስተዋፅዖ ትልቅ አገር ይገነባል!! የኢሕአደግ ሴቶች ሊግ 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በመቀሌ ከተማ ያካሄዳል፡፡ የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ ስራ አስፈፃሚ በመቐለ ከተማ ለሚያካሂደው ጉባኤ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በመገምገም ላይ ነው። ኢሕአደግ ሴቶች ሊግ 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በመቀሌ ከተማ ያካሄዳል፡፡ የአዴፓ ሴቶች ሊግ 4ተኛ መደበኛ ጉባኤ የሊጉን ሊቀመንበርና ም/ሊቀመንበር በመምረጥ ተጠናቋል!!! ክብርት ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ሆነው ተመረጡ፡፡
Back

የሶቶች ሊግ የመስክ ጉብኝት ሲያካሂዱ

ዜና ዜና

የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ የአቋም መግለጫ

"የተደራጀ የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለሁለንተናዊ ሃገራዊ ለውጥ"! በሚል መሪ ቃል በሰሜን ኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ዋና ከተማ ውቢቷ መቐለ ላይ የተካሄደው የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በሴቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሲሆን የሴቷ ተጠቃሚነት ሊረጋገጥ የሚችለው ሰላሟ ሲረጋገጥ፣ ሰላሟ ለማረጋገጥ ደግሞ ያለ ማንም ጠባቂነት ሴቷ ራሷ ለሰላሟ ጉዳይ ዘብ እንድትቋም ይህንን በህዝባዊ ተሳትፎ ለማረጋገጥ ማለት አጥፊዎችን በማጋለጥና ባጠፉት ጥፋት ልክ ህግ እንዲዳኝ በማድረግ ብሎም የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ የሚተገብር ይሆናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ በመቐለ ከተማ እያካሄደ ባለው የሊጉ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ጓዲት መሰረት መስቀሌን ከደኢህዴን በሊቀመንበርነት፣እንዲሁም ጓዲት መስከረም አበበን ከአዴፓ ምክትል ሊቀ መንበር አድርጎ መርጧል።

የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ በመቐለ ከተማ እያካሄደ ባለው የሊጉ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ጓዲት መሰረት መስቀሌን ከደኢህዴን በሊቀመንበርነት፣እንዲሁም ጓዲት መስከረም አበበን ከአዴፓ የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ ፀሀፊ አድርጎ መርጧል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ የአገሪቱን ሰላም በማስጠበቅ ሂደት ውስጥ ግንባር ቀደም ሆኖ ለመንቀሳቀስ መወሰኑ ተገለፀ

በመቐለ ከተማ እየተካሄደ ባለው 4ኛ የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ መደበኛ ጉባኤ የሰላም ጉዳይ የሊጉ ዋነኛ የመነጋገሪያ አጀንዳ የነበረ ሲሆን ሊጉ አባላቶቹንና መላውን የኢትዮጵያ ሴቶች በማነቃነቅ ለሰላም ግንባታ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ አስታውቋል፡፡ አጠቃላይ በሰላም ዙሪያ የሴቶች ሚና ምን መሆን አለበት፤ አሁንስ በአገሪቱ ያለው ተጨባጭ ሁኔታ ምን ይመስላል በሚል የመነሻ ፅሁፍ በኢህአዴግ ሴቶች ሊግ ሊቀመንበርና የሰላም ሚኒስቴሯ ጓዲት ሙፈርህያት ካሚል ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ሴቶች በአገሪቱ የሰላም እጦት በተከሰተበት ጊዜ ሁሉ ግምባር ቀደም ተጎጂዎች መሆናቸውንና ይህ ሁኔት በአፋጣኝ እልባት ማግኘት እንደሚገባው የሊግ አባላት የጋራ ውሳኔ አሳልፈዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

መጣጥፎች መጣጥፎች

ጀግኒት! ከማጀት እስከ አደባባይ

ከጥንት ከጠዋቱ የአገር ምሰሶ የቤት አለኝታ ሴት ናት፡፡ በባህልና ወግ ተጠፍንጋም ሴት ለቤቷ መሰረት ናት፡፡ ትዳር አጋሯን ጨምሮ ቁጥራቸው ይነስም ይብዛም ልጆቿን እንደአመላቸው አቅፋ ለወግ የምታበቃው ሴት ናት፡፡ የሴቶች ሁሉ ቁንጮ የሆኑት እቴጌ ጣይቱን ጨምሮ አገራችን በወጣቻቸው እና በወረደቻቸው አባጣ ጎርባጣዎች ሁሉ የአገራችን ሴቶች ግምባር ቀድም ተሳታፊዎች ነበሩ፡፡ ደጀን ከመሆን ራስን በጦር ግምባር እስከመማገድ የደረሰ ብስለትና ብቃታቸውን በተግባር አሳይተዋል፡፡

እድሉን እንጠቀምበት

ኢህአዴግ የአመራር ለውጥ ካካሄደ በኋላ ባለፉት ጥቂት ወራት የለውጥ ጅማሮዎች ታይተዋል፡፡ በአመራር ለውጡ ወቅት የተነገሩትን ቃላት በድርጊት ለመመንዘር ቀን ቀንን እስኪተካ መጠበቅ ሳያስፈልግ በየቀኑ ከሚታሰበው እና ከተለመደው በተለየ መልኩ ሁነቶች ተበራክተው፤ አዳዲስ ክስተቶች ተነባብረው ግርምት እና ስለ መጪው ጊዜ ተስፋን ጭሯል፡፡

ትንሽ በሚመስል የግለሰብ አስተዋፅዖ ትልቅ አገር ይገነባል!!

ስለ አገር ግንባታ ስናወራ መቼም ሁላችንም ወደየራሳችን ሁኔታ ጎትተን መውሰዳችን አይቀሬ ነው፡፡ ማንነታችን ቤታችን በሆነ የጋራ ጉዳይ ላይ ደግሞ ሁሌም ቢሆን የተሻለ ማሰብና ያንን ለማሳካት መጣር አንድ የወደፊቱን መተለም የሚችል ዜጋ ስብዕና ነው፡፡ አገር አገር ሆና እንድትቆም የእኔ ሚና ምን ነበር? አሁንስ ሚናዬን እየተወጣሁ ነው ወይ? ወደ ፊትስ ምን ማድረግ አለብኝ የሚል ጤናማ የእለት ተእለት አስተሳሰብ ሁሉም ሰው ቢኖረው የተሻለ አገር የመገንባት እድሉ ሰፊ እንደሚሆን መገመት አያዳግትም፡፡ ምክንያቱም አገር ሁሉም ሰው በልኩ በሚያውለው ትንሽ የምትመስል አስተዋፅዖ ልክ ይገነባልና፡፡

የሴቶች ሊግ ፕሮግራም የሴቶች ሊግ ፕሮግራም

የሴቶች ሊግ ደንብና መመሪያ የሴቶች ሊግ ደንብና መመሪያ