መጣጥፎች መጣጥፎች

ጀግኒት! ከማጀት እስከ አደባባይ

ከጥንት ከጠዋቱ የአገር ምሰሶ የቤት አለኝታ ሴት ናት፡፡ በባህልና ወግ ተጠፍንጋም ሴት ለቤቷ መሰረት ናት፡፡ ትዳር አጋሯን ጨምሮ ቁጥራቸው ይነስም ይብዛም ልጆቿን እንደአመላቸው አቅፋ ለወግ የምታበቃው ሴት ናት፡፡ የሴቶች ሁሉ ቁንጮ የሆኑት እቴጌ ጣይቱን ጨምሮ አገራችን በወጣቻቸው እና በወረደቻቸው አባጣ ጎርባጣዎች ሁሉ የአገራችን ሴቶች ግምባር ቀድም ተሳታፊዎች ነበሩ፡፡ ደጀን ከመሆን ራስን በጦር ግምባር እስከመማገድ የደረሰ ብስለትና ብቃታቸውን በተግባር አሳይተዋል፡፡

እድሉን እንጠቀምበት

ኢህአዴግ የአመራር ለውጥ ካካሄደ በኋላ ባለፉት ጥቂት ወራት የለውጥ ጅማሮዎች ታይተዋል፡፡ በአመራር ለውጡ ወቅት የተነገሩትን ቃላት በድርጊት ለመመንዘር ቀን ቀንን እስኪተካ መጠበቅ ሳያስፈልግ በየቀኑ ከሚታሰበው እና ከተለመደው በተለየ መልኩ ሁነቶች ተበራክተው፤ አዳዲስ ክስተቶች ተነባብረው ግርምት እና ስለ መጪው ጊዜ ተስፋን ጭሯል፡፡

ትንሽ በሚመስል የግለሰብ አስተዋፅዖ ትልቅ አገር ይገነባል!!

ስለ አገር ግንባታ ስናወራ መቼም ሁላችንም ወደየራሳችን ሁኔታ ጎትተን መውሰዳችን አይቀሬ ነው፡፡ ማንነታችን ቤታችን በሆነ የጋራ ጉዳይ ላይ ደግሞ ሁሌም ቢሆን የተሻለ ማሰብና ያንን ለማሳካት መጣር አንድ የወደፊቱን መተለም የሚችል ዜጋ ስብዕና ነው፡፡ አገር አገር ሆና እንድትቆም የእኔ ሚና ምን ነበር? አሁንስ ሚናዬን እየተወጣሁ ነው ወይ? ወደ ፊትስ ምን ማድረግ አለብኝ የሚል ጤናማ የእለት ተእለት አስተሳሰብ ሁሉም ሰው ቢኖረው የተሻለ አገር የመገንባት እድሉ ሰፊ እንደሚሆን መገመት አያዳግትም፡፡ ምክንያቱም አገር ሁሉም ሰው በልኩ በሚያውለው ትንሽ የምትመስል አስተዋፅዖ ልክ ይገነባልና፡፡