የኢህአዴግ ም/ቤት ጽ/ቤት ከኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ ጋር በመተባበር በባህር ዳር ከተማ ለሊግ አባላቱ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡

የስልጠናው ትኩረት የአገር ግንባታ እና በአገር ግንባታ ዘርፍ የወጣቶች ሚና ምን መሆን አለበት? የቀውስ ጊዜ የተግባቦት ስራና የወቅቱ ማህበራዊ ሚዲያ አካሄድና በውስጡ ያሉ መልካም አጋጣሚዎችና ፈተናዎችን እና መሰል ጉዳዮች ላይ ይሆናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ 4ተኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ከጥር 19 ቀን ጀምሮ በሀዋሣ ከተማ ሊካሄድ ነው፡፡

በኢሕአዴግ ወጣቶች ሊግ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ጉባኤ ከሁለት ዓመት እስከ ሁለት አመት ተኩል ጊዜ መካሄድ ይኖርበታል፡፡ በዚሁ መሰረት የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ ከጥር 19-21 /2011 ዓ.ም 4ተኛ ድርጅታዊ ጉባኤውን በሀዋሣ ከተማ ያካሂዳል፡፡ የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ ሥራ አስፈጻሚ አባልና የአዘጋጅ ኮሚቴው ቃል አቀባይ ወጣት ጫላ ኦሊቃ የጉባኤውን ዝግጅት አስመልክቶ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ጉባዔው ከእናት ድርጅቱ ጉባኤ ማግስትና ሀገሪቱ በሁለንተናዊ የለውጥ እንቅስቀሴ ባለችበት ወቅት የሚካሄድ በመሆኑ ታሪካዊና ልዩ ያደርገዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኦዴፓ ወጣቶች ሊግ 4ተኛ ድርጅታዊ ጉባኤ በአዳማ ከተማ ሊካሄድ ነው

በሊግ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ጉባኤ ከሁለት ዓመት እስከ ሁለት አመት ተኩል ጊዜ መካሄድ ይኖርበታል፡፡ በዚሁ መሰረት የኦዴፓ ወጣቶች ሊግ ከጥር 14-17 /2011 ዓ.ም 4ተኛ ድርጅታዊ ጉባኤውን የወጣቶች አንድነት ለመሰረታዊ ለዉጥ በሚል መሪህ ቃል በአዳማ ከተማ ያካሂዳል፡፡ ጉባኤውን ለማካሄድ የሚያስችል አስፈላጊው ዝግጅት ሁሉ መጠናቀቁ እና የሊግ ተወካዮችና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በደማቅ የመክፈቻ ስነ ስርዓት ይጀመራል ተብሏል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ለውጡን የሚመጥን የአመራር ስምሪት መስጠት ለምርጫ የሚቀርብ ሳይሆን ብቸኛው የለውጡ አማራጭ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ ስራ አስፈጻሚ አመራር ኮሚቴመደበኛ ስበሰባውን ባካሔደበት ወቅት የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ በከተማችን የ6 ወር ወጣት ዘርፍ ተግባራት አፈፃፀም በመገምገም ለውጡ በከተማችን አዲስ አበባ ወጣቶች ዘንድ የፈጠረውን መነሳሳት በማቀጣጠል የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ ትክክለኛ የወጣቶች የትግል መድረክ ሆኖ ለመውጣት ለውጡን የሚመጥን የአመራር ስምሪት መስጠት ለምርጫ የሚቀርብ ሳይሆን ብቸኛው የለውጥ አማራጭ መሆኑን በመግለፅ አደረጃጀቱ የአዲስ አበባ ወጣቶችን የስነ ልቦና እድገት ያማከለ የወጣቶች መሰባሰቢያ ጥላ ለመሆን መስራት

ተጨማሪ ያንብቡ…

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ወጣቶች ሊግ 4ኛ መደበኛ ጉባኤን አስመልክቶ ለተሳታፊ የሚዲያ አካላት ስለ ጉባኤው አካሄድ እና ተዛማጅ ጉዳዮች መግለጫ ተሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ እና የአዴፓ ወጣቶች ሊግ ሊቀመንበር የሆኑት ጓድ ሙቀት ታረቀኝ ናቸው። በመግለጫቸው ላይ ዛሬ ላይ ሀገራችን የተጎናፀፈችው ስኬታማ የለውጥ መስመር እውን እንዲሆን ከየትኛውም የህብረተሰብ ክፍል በላይ ወጣቱ ዋጋ መክፈሉን አንስተው ጉባኤውም በቀጣይ ወጣቶች ሀገራዊ ለውጡን በሰላማዊ መንገድ ማስቀጠል የሚችሉበትን ሁኔታ ጠቋሚ እንደሚሆን ገልፀዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

ወጣትነት ለሀገር ግንባታ

ወጣትነት ብዙ ተግባራትን የሚፈጸምበትና ሃላፊነት የሚበቃበት የእድሜ ክልል ነው ፡፡ ወጣትነት ኃይል ነው፤ ጉልበት፤ጥንካሬና ብርታት ነው፡፡ በየዘመናቱ ለተመዘገቡ ለውጦችም ይሁን ጥፋቶች የወጣቶች ሚና ላቀ ያለ ነው፡፡ በሀገራችን ውስጥ የውጭ ወራሪዎችን አሳፍሮ ከመመከት ጀምሮ በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መስኮች ወጣቶች ጉልህ ሚና ተጫውተዋል፡፡