ከሁሉ አስቀድሜ ለመላዉ የሊጋችን አባላት እና ደጋፊዎች እንኳን ለ4ተኛ መደበኛ ጉባኤየችን በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን እላለሁ

የሊጋችን 4ኛ መደበኛ ጉበኤ የሚካሄደዉ መሪ ድርጅታችንና መንግስታችን በጥልቅ ተሃድሶ ሂደት የተለዩ ችግሮችን በሁሉም ዘርፍ ተገቢዉን ምላሽ ለመስጠት እየሰራ ባለበት ወቅት እና በመላዉ የሃገራችን ወጣቶች ዘንድ ተስፋን የሚጭሩ ለዉጦች እየመጡ ባለበት ወቅት የሚካሄድ  ጉባኤ በመሆኑ የተለየ እና ደማቅ ያደርገዋል፡፡

የኦሮሞ ዴሞክራትክ  ፓርቲ ወጣቶች ሊግም እንደ ሀገር የተጀመረዉን የለዉጥ ጉዞ በተሳካ ሁኔታ እንድቀጥል መላዉን አባላቱን በመንቀሳቀስ እየሰራ ይገኛል፡፡

የግንባራችን የሊጉ አባላትም በመሪ ድርጅታችንና መንግስታችን የተጀመሩ የለዉጥ ሂደቶች በተሳካ ሁኔታ እንድቀጥል እና ከለዉጡ  የሀገራችን ወጣቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከምንጊዜዉም በላይ እጅ ለእጅ ተያይዘን በድርጅታችን የአብሮነትና ጓደዊነት መንፈስ ተየይዘን ለዉጡን ከግብ ለማድረስ እንድንረባረብ እንደ ኦሮሞ ዲሞክራትክ ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ድልና ድምቀት ለኢህአዴግ ወጣት ሊግ 4ተኛ መደበኛ ጉባኤ

ክብርና ሞጎስ ለትግሉ ሰማዕታት